Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ወገን ለወገን በሚል የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አድርጓል።

0 668

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ወገን ለወገን በሚል የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አድርጓል።የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል አርብቶ አደር አካባቢ በሆኑት የቦረና እና ምእራብ ጉጂ አካባቢ በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ነው ድጋፉን ያደረገው።ድጋፉም 5 ሺህ ኩንታል ስንዴ እና አካባቢው ካጋጠመው ድርቅ እስኪያገግም ድረስ የሚያገለግሉ ሁለት የውሃ ማመላለሻ (ቦቴ) ተሽከርካሪዎች ናቸው።

oro_amahara_1.jpg

የአማራ ክልል የመንግስት ኩሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የክልሉን መንግስት በመወከል ድጋፉን ስፍራው ድረስ በመጓዝ አስረክበዋል።በዚሁ ጊዜም የአማራ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ወዳጁ ለሆነው ለኦሮሞ ህዝብ ያደረገው ድጋፍ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋም ከአማራ ክልል ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከቦረና ዞን መንግስት ኮምዩኒኬን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy