የኢትዮዽያ ፈርስቱ ቢንያም ከበደ – ወዴት እየሄድክ ነው?( Begashaw K)
ለረጅም ዓመታት ተከታትዬሃለሁ። ስለብርጭቆው ግማሽ ውሃ መያዝ እንጂ ስለብርጭቆው ግማሽ ባዶ መሆን ማውራት የማትወድ ሰው የነበርክበትን ዘመን በደንብ አስታውሰዋለሁ። ሆኖም ፣ እንደሰራ አይገድል እንዲሉ ፣ በውል ባልተረዳሁት ምክንያት ላለፉት የተወሰኑ ጊዜያት ያለህ አቋም በግልጽ ተለውጧል። አጥር ላይ ሆነህ ከዚህ እና ከዚያ የወገኑ ዘገባዎችን እይታዎችን በማቅረብም ነበር የቀደመ ቦታህን መልቀቅ የጀመርከው። ይሄንን ሁናቴ/አካሄድ “ምናልባት ኢህአዴግ ባይሆንለት እና ተቃዋሚው በለስ ቢቀናው ፣ ተቃውሜም ነበር እኮ” ለማለት እና ሚዛናዊ ለመባል የከፈልከው ዋጋ አድርጌ ወስጄው ነበር። ይህ አካሄድ ቀላል ቁጥር የሌላችውን እና የት ይደርሳሉ የተባሉ ደጋፊዎችን ሰለባ ያደረገ አካሄድ በመሆኑ ብዙም አልፈረድኩብህ ነበር። በስተመጨረሻ ላይ ያመጣህው የጭቃ ጅራፍ እና ኢሃዴግን አንድም መልካም ስራ የሌለው እና ሃጢያቱ የበዛ ድርጅት የማድረግ ጥረትህ ግን ፣ በግልጽ ከእጥር ላይ መውረድህን እና ኢሳቶችን የሚያስንቅ ስራ እየሰራህ መሆኑን አርድቶኛል። ከልብ የማዝነው ለአንተው እንጂ ፤ በፈተና ተጸንሶ ፣ በፈተና ተወልዶ ፣ በፈተና ያደገው እና እዚህ የደረሰው ኢህአዴግ በእንተ ሌላኛውን ጎራ መቀላቀል የሚደርስበት ቅንጣት ታህል ጉዳት የለም። በትግሉም ሆነ ከድል በኋላ ባለው ታሪኩ የምንረዳው ፣ ፈተናዎች ይበልጥ ኣስተምረውት እና አጠንክረውት የሚነሳ ድርጅት እንጂ ወድቆ የሚቀር አለመሆኑን ነው።
በርካታ እና እሳፋሪ የሆኑ መሰረተ ቢስ ውንጀላዎችን በዚህ ስርዓት እና በመሪዎቹ ላይ መንዛቱን ስራዬ ብለህ ተያይዘህዋል። ለአብነት የተወሰኑትን ላንሳ እና ፤ ካለፈው ሃገራዊ ምርጫ ቀደም ብሎ ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ተገኝተህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መግለጫ ስትከታተል እና ዕድል ተሰጥቶህ ጥያቄ አቅርበህ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማሳፈር ሞክረህ እራስህን ያሳፈርክበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። በእዛን ሰዓት ህዝቡ በኢህአዴግ ክፉኛ መማረሩን እና በሚቀጥለው ምርጫ ድርጅቱ በዝረራ ይሸነፋል የሚል ስጋትህን ገልጸህ ነበር። ከህዝቡ ምሬት ምክንያቶች አንዱም ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ያለዉ የውሃ እጥረት ጉዳይ ነበር። በአንተ አገላለጽ ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብ ጀሪካን ይዞ ውሃ ፍለጋ ከላይ እታች ሲሯሯጥ መዋል ነበር ስራው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በተለመደ ረጋ ያለ ንግግራቸው ፣ የከተማው 75% ነዋሪ 100% የማይቛረጥ የውሃ አገልግሎት የሚያገኝ መሆኑን እና የተቀረውን 25% የሆነውን ነዋሪም ችግር ለመፍታት ምን ምን ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ መረጃ ሰጡህ። ምንም እንኳን የልምድ ጋዜጠኛ ብትሆን ፣ የተወሰኑ የቤት ስራዎችን ሰርተህ መሄድ ሲገባህ ፣ ያንን ሳታደርግ በመቅረት ያቀረብከው ጥያቄ ሞኝ አስመሰለህ። የምርጫውም ውጤት እንደ አንተ ሟርት ሳይሆን ፣ በዝረራ ተሸናፊው ሌላው ሆነ። በወቅቱም ፣ የመንግስትም ሆነ የብዙዎች ደጋፊዎች ጭንቀት ‘ኢህአዴግ ያሸንፍ አያሸንፍ ይሆን?” የሚለው ሳይሆን ፣ የተገኘው ውጤት እንዳይገኝ ፣ ማለትም “ኢሀዴግ ሙጥጥ አድርጎ መቀመጫዎቹን እንዳይወስድ” የሚል ፍርሃት ነበር – የሚመጣው ትችት ይታወቅ ነበርና። በመጨረሻው እይታህ/ብዥታህ አስተካክለህ ለተቃዋሚው ውጤት አልባነት የመጀመሪያው ተጠያቂ እራሱ ተቃዋሚው እንደሆነ ደፍረህ እውነቱን ተናገርክ እንጂ ፤ ቀደም ባለው እይታህ/ብዥታህ “ለተቃዋሚው ውጤት አልባነት ተጠያቂው ኢህአዴግ መሆኑን” ልታስረዳንም ሞክረህ ነበር።
ሰማእታቱም ዛሬ ቀና ብለው ቢያዩ ስለሚሰማቸው ስሜት የገመትከውም ፣ የትናንቱን ብሩህ መነጽር አውልቀህ መጣልህን እና የድፍን ጥቁር መነጽር ተጠቃሚነትህን ያረጋገጥኩበት አንዱ አጋጣሚ ነበር። ሰማእታቱ ዛሬ ቀና ብለው ምድራችንን ቢያዩ ብዬ ሳስብ ፣ የእኔ ፍርሃት ፣ ሌላ ሃገር የገቡ እንዳይመስላቸው ነው። ከመቀለ/ኮረም እስከ ሃዋሳ/ይርጋዓለም ፤ በመላ ሃገሪቱ ከተማም ሆነ ገጠር አካባቢ ከ25 ዓመት በፊት ቀርቶ ፣ ከ5 እና ከ10 ዓመታት በፊት ምድሪቱን ያየ ሁሉ በመደነቅ መሞላቱ እይቀሬ ነው። በሰዉም ሆነ በምድሪቱ ላይ የሚታይ እና የሚዳሰስ ለውጥ አለ ፤ ዓይኑን ለጨፈነ ወይም ድፍን ጥቁር መነጽር ተጠቃሚ አውቆ-እውር ካልሆነ በቀር። መቀሌ ላይ የግል ጋዜጣ የማይታይበት ምክንያትስ ፣ በመንግስት ትዕዛዝ ስለተከለከለ ወይስ በሌላ ምክንያት? (የጋዜጣ ማንበብ ልምድ እና ፍላጎት ማጣትን ጨምሮ።) ፈርስን ውሃ ዳር ማድረስ እንጂ እንዲጠጣ ማድረግ አይቻልም እንዲሉ ፣ የመንግስት ሃላፊነት ዕድሉን መክፈት እንጂ ቀሪው የህዝብ ፍላጎት እና አቅርቦት ጉዳይ ነው። ሰማእታቱ ቀና ብለው ቢመለከቱ ፣ የድርቅ እና የእልቂት ቁርኝት/ጋብቻ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍረሱን ሲመለከቱ ፣ ህጻናት የ5 ዓመት እድሜን አልፎ የመኖር እድላቸው በአስገራሚ ቁጥር መጨመሩን ሲያዩ ፣ የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነው ድህነት ዓለምን ባነጋገረ ፍጥነት መቀነሱ ፣ በታላቅነቱ በአህጉሩ የበላይነትን ስፍራ የያዘው የህዳሴ ግድብ ወደመገባደድ እየሄደ መሆኑን ፣ የቱን አንስቸ የቱን ልተወው – ይሄ ሁሉ ወደ ተዓምር የወሰደው ለውጥ እና እድገት በሩብ ምዕተ ዓመት ዕድሜ ተከናወኖ ሲያዩ የሚሰማቸዉን ደስታ ለመገመት ያዳግተኛል። መንፈስ ናቸው እና ፣ በተለይም ደግሞ ትግሉን እና መስዋዕትነቱን ከእኛ ቀድመው የጀመሩትን እና ከእኛ አኩል ነጻ የወጡትን የኤርትራውያንን ሁኔታ ብቅ ብለው ቢመለከቱ ፣ ለፍቶ መና መሆንን በተግባር አይተው እና የኢትዮዽያ እጣ ፈንታ ያ ባለመሆኑ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሲሆን ይታየኛል።
በመጨረሻው እይታህ/ብዥታህ፣ ይሉኝታ በሌለው ሁኔታ ኢህአዴግን ጨርሶ ዋጋ ቢስ ለማድረግ ብዙ ጥረሃል። አንዱ ችግርህ ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ መሆኑ ነው። በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የአንድ ጎሳ ተወላጆች በድጋሚ በወገኖቻችን ላይ ጥቃት የማድረሳቸውን አሳዛኝ ክስተት በኢህአዴግ ቸልተኛነት የተፈጸመ እና በቀላሉ ማስቆም እንደሚቻል ተናገርክ። እንዴት ይደረግ? ሰራዊታችንን አዝምተን የደቡብ ሱዳንን ህዝብ እንጨፍጭፍ? ወይስ ያንን ሁሉ ረጅም ድንበር ፣ አንድም ክፍት ቦታ ሳይቀር በወታደር እንጠር? ምናልባት ከአመሪካው ፕሬዝደንት ሃሳብ ተውሰን ትልቅ ግንብ እናቁም? በናይጄሪያ ግዛት ውስጥ ተንሰራፍቶ ናይጄሪያን እያስጨነቀ ከሚገኘው ቦኮ ሃራም ጋር ለማወዳደር እና እንደውም የእኛው የባሰ ሞኑንም ትንሽ ሳታፍር ልትነግረን ሞከርክ። መቀመጫዉን ሌላ ሉአላዊ ሃገር ላይ ያደረገ እና ሰርጎ እየገባ ጥቃት የሚፈጽም እና በውል ያልታወቀ መገኛ ስፍራ የሌለዉን የጥፋት ሃይል በቀላሉ መቆጣጠር እና ማጥቃት እንዴት እንደሚቻል ብታስረዳን መልካም ነበር። በትግራይ እና በኤርትራ መሃል በሚገኘው ድንበር አካባቢም እንዲሁ ፣ ዘጎቻችን ሰርተው መብላት የሚችሉብት ምንም ስፍራ አለመኖሩንም ነግረህናል። በእዛ እጅግ ሰፊ በሆነ ድንበር ያለዉን ሁኔታስ እንዴት ነው እንዲህ ጥርት ባለ ሁኔታ ያወቅከው? ግምት? የሰው ወሬ? በአካባቢው እና በአጠቃላይ ሃገራችን ላይ ሻቢያ የሚፈጥረውን መልካም ያልሆነ ተጽእኖ አልረዳም ማለት አይደለም። ሆኖም ግን የኤርትራን መንግስት መቀየር ውይም በስቃይ የሚኖረውን የኤርትራ ህዝብ የሚጎዳ ጥቃት መፈጸም ለረጅሙ ሰላም እና የመረጋጋት ሂደት የተሻለ ፍጻሜ የማስገኘቱ ጉዳይ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? በዚህ ዘመን አምባገነን ስርዓቶችን አስወግደው ወደ ከፋ እና መዉጫ የሌለው ችግር ዉስጥ የገቡ በርካታ ሃገራት ጉዳይ ትምህርት ሊሆነን ይገባል።ሩቅ ሳንሄድ ፣ በምስራቅ እና በምዕራብ በኩል ያሉን ጎረቤቶች የገቡበትን የከፋ ቀውስ መመልከት ይቻላል። መንግስታችንም ከረጅም ትዕግስት እና ማስተዋል የተሞላው ጉዞ በኋላ እና ያለፉት ኣካሄዶች ያስገኙት ውጤት የሚያረካ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ሌላ አዲስ መንገድ ለመከተል ሁኔታዎችን አያጠና እና እየተዘጋጀ ባለበት እና ባለቀ ሰዓት ተነስተህ ለህዝብ ተቆርቋሪ መስለህ ለመታየት መሞከር፣ ትዝብት ያተርፍልህ ይሆናል እንጂ ከኢህአዴግ በላይ የህዝብ ወገንተኛ አያደርግህም።
ቆሼ በሚባለው አካባቢ ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ ለሰነዘርካቸው ሌላ አሳፋሪ አስተያየቶች ጥቂት ልበል። አንድን ትልቅ ቆሻሻ ከተማ ተረክቦ ወደሚደነቅ ውብ ከተማነት በፈጣን ሁኔታ በመቀየር ሂደት ላይ ያለን የከተማ አስተዳደር እና መንግስት “እዚህጋ የጎደለ ነገር አለ” ፣ “ይህስ ለምን ቀድሞ አልተሰራም” ብሎ ለመተቸት የሚያስችል ድፍረት ከየት እንደሚመጣ ማወቅ ይቸግረኛል። ይህ መንግስት የተረከበውን የተንኮታኮተ የኢኮኖሚ አቅም እና የከፋ የድህነት ደረጃ ተረሳ ወይስ በምን ሂሳብ ነው ‘አንዴት ይህ አልተሰራም?’ ተብሎ ለቁጣ የሚያስነሳው? ዛሬም ቢሆን ድህነቱ በአስተማማኝ ሁኔታ እየተመታ ነው እንጂ ገና ብዙ ይቀረናል። ይህ ለአሳዛኝ ሁኔታ ምክንያት የሆነው እና ለ50 ዓመታት ሲከመር የኖረ ቆሻሻ ከየት እንደተነሳን ጥሩ ማሳያ ነው። የብዙ ምዕተ ዓመታት ውዝፍ ስራን ለመስራት 25 ዓመታት ብዙ ናቸው ብሎ ማሰብ ፣ ከትልቅ ይቅርታ ጋር ፣ ትልቅ ድንቁርና ነው። ዛሬ እንደምሳሌ የምናያቸው በለጸጉ የሚባሉ ሃገራት በዕድገት እና የአዲስ ስርዓት ጉዟቸው በ25 አይደለም በ100 እና ከዛም በላይ አመታቸው ምን ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ለመረዳት መሞከር ተገቢ ሊሆን ይችላል። ዛሬም ቢሆን ፣ ከዚህ ሁሉ የእድገት እና የለዉጥ ጉዞ በኋላ የአሉበት ሁኔታ አልጋ ባልጋ ከመሆን ብዙ የራቀ ነው። የቆሼው አደጋ በተከሰተበት ወቅትም 39,000 የኮንዶ መኖሪያ ቤቶች ፣ በጣም ዝቅተኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ለአላቸው የከተማ ነዋሪዎች ያስተላለፈ (በአማካይ 200 ሺህ የከተማው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ተግባር) እና ለሎች እጅግ መጠነ ሰፊ የሆኑ አኩሪ ለውጦችን ያመጣ አስተዳደር ፤ ከቀደሙት ስርዓቶች ከወረሳቸው ችግሮች በአንዱ ላይ በደረሰ ድንገተኛ ኣደጋ በወንጀል ይጠየቅልኝ ብሎ ማለት (ያዉም ከወሬ የዘለለ ለሃገሩ ለውጥ ቅንጣት አስተዋጽኦ ባላደረገ ግለሰብ) እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። አዎ ፣ ሰውን ካለፈ/ከሞተ በኋላ እንጂ በቁም ማመስገን ልማዱ የለንም። ሰማዕታቱ ምንኛ ታድለዋል ፣ በህይወት ቢኖሩ እኮ የእነሱም እጣ ፈንታ ከጓዶቻቸው የተለየ አይሆንም ነበር። ከበርካታ የአዲስ አበባ መስተዳድር እና ፌደራል መንግስቱ አኩሪ ድሎች መሃል በቅርቡ በስራ ላይ የሚዉለው አና በከፋ ድህነት ላይ የሚገኙ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የማህበራዊ ደህንነት ድጎማ ክፍያ ይገኝበታል። ለዚህ ሁሉ ስኬት ያበቃን ገንዘብ ከየት ተገኘ? የሚለው ጥያቄ ተገቢ ሊሆን ይችላል እንጂ ፣ ይህ እንዴት ጎደለ ብሎ መቆጣት የገዛ ማንነትን አለማወቅ ነው እላለሁ። ሃገሪቱ ገንዘብ መያዝ ከቻለችባቸው ምክንያቶች አንዱ ፣ በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርተው ሌት ተቀን የሚተጉ ዋጋ ከፋይ ዜጎችን ከጊዜው ጋር በማይሄድ ዝቅተኛ ክፍያ በማሰራት እና የተገኘውን ገንዘብ መልሶ ለልማት በማዋል ነው። ይህንን ስል የማይገባቸውን ጥቅም የሚያገኙ እና ርካሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች የሉም ለማለት ሳይሆን ፣ ይሄ ሁሉ ስኬት የመጣው ሁሉም ሌቦች በሆኑበት ስርዓት ያለመሆኑን እና ክብር እና ምስጋና የሚገባቸው አገልጋዮችም እንዳሉን ለመጠቆም ነው።
ድሪባ ኩማን የመሰለ ትጉህ እና ሰርተው ማሰራት እንደሚችሉ በሰፊ ተግባር ያሳዩ መሪን ማመስገን ባይሆንልን ወንጀለኛ ለማለት መድፈር ከፍያለ ነውር እና ወንጀል ነው። አደጋው ከተከሰተ በኋላም የሰጡት አመራር ፣ መልካም መናገር የማይሆንላቸውን ተቃዋሚዎች እንኳን እንዲያመሰግኑ አስገድዷል።
የተከሰተው አሳዛኝ አደጋ ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ ብሄራዊ ሃዘን ነበር። የመንግስት የብሄራዊ ሃዘን አዋጅ መፈጸም ያለበት ስርዓት እንጂ በደረሰው ሃዘን ላይ የሚያመጣው ወይም የሚለውጠው ቅንጣት ነገር የለም። የሃገሪቱን የፓርላሜንታዊ ደሞክራሲ ስርዓት ተከትሎ ፣ አዋጁ በህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት እንዲታወጅ ለማድረግ ጥቂት ቀናት ወሰደ። የምንከተለው ስርዓት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወይም ሌላ የበላይ አካል የመሰለዉን አዋጅ ማውጣትን የሚችልበትን አቅም የሚሰጥ አይደለም። አደጋው ከደረሰበት ሰዓት እና ቀን ጀምሮ በስፍራው የተገኙት ከፍተኛ ባለስልጣኖች በርካታ መሆናቸውን ወደ ጎን ትቶ ፣ ከአራት ቀን በኋላ ለቅሶ ስለደረሱት የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ማውራትን መምረጥ ከኢሳት የባሱ ኢሳት መሆን ይሉሃል ይሄ ነው። ፕረዝደንቱ እንዳሉት አደጋው ለትንሽ ቀደማቸው እንጂ የከተማው አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ላይም ተጨባጭ የሆነ ስራን እየሰራ እንጂ እጁን አጣምሮ የተቀመጠ አልነበረም።
በመጨረሻም ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ጋር በነበራቸው የረጅም ሰዓታት ቆይታ/ውይይት ፣ አንዲት አረፍተ ነገርን መዘህ በማውጣት የሃገራችንን ደሞክራሲ ሞት ልታረዳን ተነሳህ።
ቤን ሙት ፣ እኔም በተራዬ ኣፈርኩልህ/አዘንኩልህ። ለመሆኑ የሃገሪቱ መሪ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑበትን ምክንያት ለማወቅ ሞክረሃል? ጉዳዩ በፍርድ ስርዓቱ የተያዘ ከሆነ ፣ ዝርዝር መረጃ የመስጠት መብት እንደሌላቸውስ ታውቃለህ? አንተ ረጅም ዓመታት በኖርክበት ሰሜን አሜሪካስ ፣ በመሪነትም ይሁን በተለያየ ደረጃ ያሉ ባለስልጣኖች ከፍተኛ ትኩረት ባላቸው ወይም በህግ አግባብ እየታዩ ባሉጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች “ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ኣይደለሁም” ብለው ጥያቄዎችን የሚመልሱበት ሁኔታ የተለመደ ኣይደለም? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን በዝርዝር ያልገቡበት በበቂ ምክንያት እንጂ እንደው ላለመናገር ያህል እንዳልሆነ በመረዳት ከሆነስ የምክርቤቱ አባላት ታሪኩ በዝርዝር ካልተነገርን ያላሉት? አያይዘህም ፣ “ከ547 አባላት 1ም ሰው ደብዳቤ ጽፎ አልተቃወመም” አልከን አንዴት አውቅህ? እዚህጋ ኢሳቶች ትንሽ ሳይበልጡህ ኣልቀሩም – እነሱ ቢሆኑ “አንድ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱ የፓርላማ አባል 546ቱን ቀሪ አባላት አነጋግረው ደብዳቤ ጽፎ የተቃወመ እንደሌለ ገልጸውልናል” ይሉን ነበር kkk።
ዴሞክራሲ ባደገባቸው ሃገራት የአንድ ፓርቲ አባላት በአንድ መስመር የመሄድ ግዴታ እንዳለባቸውስ ረስተህው ይሆን? ለማስታወስ ይረዳህ ዘንድ የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ካናዳ ውስጥ የነበረ ኣጋጣሚን ላንሳልህ። ጆን ኑንዚያዳ የተባለ የፈደራል ፓርላማ አባል የመንግስቱን ዓመታዊ የበጀት ረቂቅ እቃወማለሁ ብሎ ድምጹን በመስጠቱ ከፓርቲው የመሰናበቱ ዜና በሰፊው የተዘገበ ስለነበር የምትረሳው አይመስለኝም። የፓርቲው አላማ እና አካሄድ ያልተስማማው አባል ፓርቲውን ለቆ መሄድ እንጂ ፓርቲው ውስጥ ሆኖ የስራ እንቅፋት መሆን የለበትም የሚል አጠቃልይ እምነት መኖሩ እንደ ፓርቲ ለውጤት መብቃት የሚያስችል ስራ ለመስራት ወሳኝ ነው። እንጂ ፣ ዛሬ አንተ እንዲህ እንዳሻህ መናገር የቻልከው ሙት ሳይሆን ህያው ዴሞክራሲ በመኖሩ ነው። ትናንት አንድ ተራ ሰላይ ወይም ካድሬ የነበረው ዜጎችን ያለፍርድ የማሰር እና የመፍታት ስልጣን ፣ ዛሬ አንድ ከፍተኛ የሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣን የለዉም ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ። ከነዋሪዎቹ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በጣም ጥቂት የሚባሉ አንባቢዎች ባሉባት አዲስ አበባ ከተማ ላይ በየመንገዱ ተዘርግተው የሚታዩ የግል ጋዜጦች እና መጽሄቶች ሙት ዴሞክራሲን አያሳዩም። በገጠርም ሆነ በከተማ በህዝብ እና በከፍተኛ አመራሮች መሃከል የሚካሄዱ ውይይቶችን የተመለከተ ፣ ዴሞክራሲውን ሙት ብሎ ለመጥራት ይቸገራል።
ቤን ወንድሜ ፣ ትንሽ የማዝነው እና የሚያሳስበኝ ጤንነትህንም መጠራጠሬ ነው። አተኩሬ ስመለከትህም ዮኒ ማኛ የሚሉትን የዓይምሮ ህሙም ሁኔታዎች አይቼብሃለሁ። ግምቴ ስህተት እንዲሆን እመኛለሁ። እዉነት ከሆነም እግዜር እንዲምርህ እመኛለሁ ፣ በጸሎትም አስብሃለሁ።
Prev Post
Leave A Reply
Cancel Reply This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos
I agree 100% on the comment above. Ben, you need to stop check yourself. I was your supporter for the last ten years, since you were here in Canada, But now you are totally changed and I also changed my support for you. It looks like you are working for ESAT. I am very sorry for what happened to you.
Biniam, I am really disappointed for what you became the member of loosers