Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ አየር መንገዶች መንገደኞችን መቀባበል ሊጀምሩ ነው

0 1,463

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ መንገደኞችን ለመቀባበል የገቡትን ስምምነት በመጭው ክረምት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተገለፀ።

አየር መንገዶቹ መንገደኞችን ለመቀባበል ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ስምምነት አድርገው ነበር።

ይህ ስምምነት የአየር መንገዶቹ ደንበኞች በአንድ ቲኬት ብቻ የጉዞ በረራ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።

ስምምነቱ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከሩ ባሻገር የመዳረሻ በረራ አቅማቸውን እንደሚያሳድግም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የድርጅቱ የስትራተጂክ ዕቅድ ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ሽፈራው እንደተናገሩት፥ ስምምነቱ በሁለቱ አየር መንገዶች የሚሳፈሩ ደንበኞችን ወደ ተለያዩ መዳረሻ አገራት ሲበሩ በሰዓትና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች የተሻለውን አማራጭ መርጠው እንዲጓዙ ያስችላል።

በተጨማሪም በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እንዲሁም በቱሪዝም በአፍሪካና በአለም ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት አቶ ግርማ።

የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ የንግድ ተጠባባቂ ኃላፊ አሮን ሙንተሲ በበኩላቸው፥ “በአፍሪካ በትርፋማነትና በፈጣን ዕድገት ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ወዳጅነታችን በማጠናከራችን ደስተኞች ነን” ብለዋል።

የመንገደኞች ቅብብሎሽ አገልግሎት ስምምነት የጋራ ደንበኛ ለሆኑ ተሳፋሪዎች ከነባር መዳረሻዎች በተጨማሪ ደርባን፣ ኬፕታውን እና ቶሮንቶ እንዲጓዙ የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል።

የመንገደኞች ቅብብሎሽ ስምምነቱም ወደ ተለያዩ የበረራ መዳረሻ አገራት እንደሚያድግም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ 95፤ በአገር ውስጥ ደግሞ 20 መዳረሻዎች አሉት።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy