Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦህዴድ 27ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነገ ይከበራል

0 338

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) 27ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በክልል ደረጃ በነገው እለት ይከበራል።

ለኦሮሞ ሕዝብ ተጠቃሚነት በተሃድሶ የገባውን ቃል ተግባራዊ በማድረግ የህዝብ ወገንተኝነቱን እንደሚያረጋግጥ ድርጅቱ አስታውቋል።

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ ባለፉት ዓመታት በውስጥና በውጭ ያጋጠሙትን እንቅፋቶች ለማስወገድ የትክክለኛ ትግል መስመሩን የህዝብ ማድረግ ላይ አትኩሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኦህዴድ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ጋሻ በመሆን ለዘመናት የማይዘነጋ ታሪክ ያስመዘገበ ድርጅት መሆኑንና ራስን በራስ በማስተዳደር ረገድ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የሰላም እና የኦሮሞ ሕዝብ የሉዓላዊነት ጥያቄዎች ላይ ፅኑ አቋም ያለው መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ብሏል።

ከህዝባችን ጋር ሆነን ያስመዘግብናቸውን ድሎች በልበ ሙሉነት ስንገልፅ ለዘመናት ካሳለፍነው ታሪክ ጋር በማነፃፀር ነው ያለው የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ፥ ከሁሉም በላይ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን እና ዴሞክራሲያዊ ባህሉን ይዞ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ እንደሚንቀሳቀስ አስታውቋል።

ድርጅቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የክልሉ ህዝብ፣ የድርጅቱ አባላት እና ደጋፊዎቹ በተለመደው ሁኔታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy