Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የክብር ዶክትሬት ጥያቄ

0 649

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አንድ ባለጸጋ በአካባቢያቸው ወደሚገኝ አንድ ኮሌጅ ጎራ ይሉና ለተቋሙ 1ሚ.ብር ለመለገስ እንደሚሹ ይናገራሉ፡፡ “ነገር ግን በአንድ ቅድመ-ሁኔታነው÷ ይኸውም የክብር ዶክትሬት የሚሰጠኝ ከሆነ ነው” ይላሉ፡፡ የኮሌጁ ፕሬዚዳንትም፤ “ታዲያ ምን ችግር አለ፤ ይሰጥዎታላ” ይላቸዋል፡፡

“የክብር ዶክትሬቱ ግን ለአህያዬ ነው” አሉ፤ ባለጸጋው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በድንጋጤና በአግራሞት መሃል ሆኖ፤ “ለአህያዬ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
ባለጸጋውም፤ “አዎ— አህያዬ ለብዙ ዓመታት እኔን ተሸክማ ከቦታ ቦታ በመውሰድ ከባድ ውለታ አድርጋልኛለችለዚህምየትራንስፖርትየክብርዶክትሬት እንዲሰጣት እሻለሁ; በማለት ኮስተር ብለው አስረዱ፡፡

“ግን እኮ—- ኮሌጃችን ለአህያ የክብር ዶክትሬት ሰጥቶ አያውቅም” አለ ፕሬዚዳንቱ፡፡
“እንግዲያውስ ገንዘቡን ለሌላ ተቋም እለግሰዋለሁ” አሉና ከመቀመጫቸው ተነሱ-ባለሃብቱ፡፡
ዓይኔ እያየ 1ሚ.ብር ሊያመልጠኝ ነው ብሎ ያሰበው ፕሬዚዳንት፤ “ቆይ እስቲ ከኮሌጁ ቦርድ ጋር ልማከርበት” ሲል ጥቂት ጊዜ እንዲሰጡት ይጠይቃል፡፡ ባለጸጋው፤ “በል በቶሎ አሳውቀኝ” ብለውት ይሄዳሉ፡፡
(በልባቸው “ብትማከር ነው የሚሻልህ” ሳይሉት አይቀሩም!)

ፕሬዚዳንቱ፤ ወዲያው የኮሌጁን ቦርድ አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራና በጉዳዩ ላይ ውይይት ይጀምራሉ፡፡ ብዙዎቹ አባላት የገንዘቡ መጠን የፈለገውን ያህል ብዙ ቢሆን፣ ለአህያ የክብር ዶክትሬት አንሰጥም ብለው ተፈጠሙ፡፡ አንድ በኮሌጁ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ብልህ አዛውንት ግንለፕሬዚዳንቱየተለየ ሃሳብ አቀረቡ፡፡

“ገንዘቡን ተቀበልና ለአህያዋ የክብር ዶክትሬቱን ስጥ ባክህ; አሉት፡፡
ፕሬዚዳንቱም ደንገጥ ብሎ፤ “ይሄን ማድረግ ለኮሌጃችን ውርደት አይሆንም?” ሲል ጠየቃቸው፡፡“በፍጹም አይሆንም; አሉ አዛውንቱ፤ “እንደውምክብር ነው፤ ለምሉዕ አህያ የክብር ዶክትሬት ስንሰጥ በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያችን ይሆናል!!” (እስከዛሬ ድረስ ከአህያ ለማይሻሉ ሰዎች ስንሰጥ ከርመናል ማለታቸው ነው!!) admas

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy