የግብጽ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን እንደ አወሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 አደባባይ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል በሚል ከቀረበባቸው የክስ ወንጀል በነጻ እንዳሰናበታቸው ተሰማ፡፡ስድስት አመት በፈጀው የክስ ሂደት የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድቤት በሰጠው የመጨረሻ ብይን ሙባረክን ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡ሙባረክ ሁለት የወንጀል ክሶች የቀረበባቸው ሲሆን፥ክሶቹም እንደ አውሮፓውያን በ2011 የጥር 25 አብዮት ወቅት ለ18 ቀናት አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ አድረገዋል በሚል እና በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ነበር፡፡በ2012 ፍርድ ቤት ሙባረክን ጠፋተኛ በመሆናቸው የእድሜ ልክ የእስር ፍርድ የሰጠ ቢሆንም ፥ ይግባኝ በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ክሱን መርምሮ ጥፋተኛ አይደሉም በሚል እንዲለቀቁ አዟል፡፡የ88 አመቱ ሙባረክ ከታሰሩ በኋላ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት በወታደራዊ ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆነው ነበር፡፡በሁለተኛው የሙስና ወንጀል ክስ እሳቸውን ጨምሮ በሁለት ወንድ ልጆቻቸው ላይ የ3 አመት የተፈረደባቸው ቢሆንም፥ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ታስቦላቸው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ በይኗል፡፡አብዛኛዎቹ የወጣቶች ና የኃይማኖት መሪዎች ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ ተፈርዶባቸው በእስር ይገኛሉ፡፡60 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከግብጽ አብዮት ጋር በተያያዘ እስር ላይ መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ FBC
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos