Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ደቡብ አፍሪካ በፕሬዚዳንት አልበሽር ምክንያት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች

0 513

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ደቡብ አፍሪካ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን አሳልፋ ባለመስጠቷ ምክንያት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ልትቀርብ ነው።

በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በደቡብ አፍሪካ በሚገቡበት ጊዜ ሀገሪቱ ፕሬዚዳንቱን አሳልፌ አልሰጥም በማለቷ ነው ፍርድ ቤት የምትቀርበው።

ፕሬዚዳንት አልበሽር ከሁለት ዓለም በፊት በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ላይ ለመካፈል በሄዱበት ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንቱን በቁጥጥር ስር እንድታውል ተጠይቃ እምቢ ማለቷ ይታወሳል።

ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንቱን በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ቤቱ አሳልፋ መስጠት ያልቻለችበትን ምክንያትም የፊታችን መያዝያ ወር ላይ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርባ ማብራሪያ እንደትሰጥም ቀጠሮ ተይዞላታል።

ደቡብ አፍሪካ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015 ላይ ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ አባልነት የመውጣት እቅድ እንዳላት አስታውቃ ነበር።

ሆኖም ግን የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እቅዱ ህገ መንግስታዊ አይደለም በማለት ውድቅ እድርጎባታል።

ምንጭ፦ CGTN Africa

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy