Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጉንፋን የማይከሰትበት ወቅት እና ቦታ የለም፡፡

0 1,597

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጉንፋን የማይከሰትበት ወቅት እና ቦታ የለም፡፡በአሜሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት እስከ ሶስት ለሚሆኑ ጊዜ 200 ዓይነት የጉንፋን ቫይረሶች ይከሰታሉ፡፡
ጤናማ ያልሆኑ ተግባራትም ጉንፋንን ሊያባብሱ ችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ጉንፋን ለረዥም ጊዜ በሰዎች የመተንፈሻ አካላት እንዲቆይ እና ጉዳቱ እንዲያመዝን ያደርገዋል፡፡በመሆኑም ጉንፋን የያዛቸው ሰዎች እንዳይባባስባቸው የሚከተሉትን ስምንት ነገሮች ከማድረግ ቢቆጠቡ መልካም ነው፡፡

1. ለጉንፋን ከመጠን ያለፈ መድሃኒት መጠቀምሰዎች ጉንፋን በያዛቸው ጊዜ ቶሎ እንዲለቃቸው በማሰብ በርካታ ልማዳዊም ሆነ ዘመናዊ ህክምናዎችን ይወስዳሉ፡፡በአፍንጫ ውስጥ የሚጨመሩ ጠብታዎችን የመሳሰሉ ተግባራት ጉንፋኑን ለጊዜውም ቢሆን ሊያስታግሱ ይችላሉ፤ ሆኖም ከመጠን በላይ የሆነ አጠቃቀማቸው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስር እንዲሰድ ያደርጉታል ነው ያሉት የአሜሪካ ብሔራዊ የጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች፡፡የአፍንጫ ጠብታን በቀን ከሶስት እስከ አራት ጊዜ መጠቀም የአፍንጫ የውስጥ ክፍል እንዲያብጥ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ከጉንፋን መባባስ ባሻገር የመተንፈሻ አካላት ህምመን እንዳያስከትሉ የአጠቃቀም መመሪያዎችን መከታተል እና ሀኪምን በማማከር መውሰድ ተገቢ ይሆናል፡፡2. አብዝቶ መጨነቅከፍተኛ ጭንቀት የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳክማል፤ በጉንፋን የተያዙ ሰዎች በተጨነቁ ቁጥር የጉንፋንን እድሜ የማራዘም እድል ያመቻቻሉ፡፡በመሆኑም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች አዕምሯቸውን መዝናናት፣ በረዥሙ መተንፈስ፣ የመንፈስ መረጋጋትን ማምጣት፣ እንደዮጋ ያሉ ስፖርቶችን በመስራት ሰውነትን ማፍታታት እና ተመስጦ ማድረግን የዘወትር ተግባራ በማድረግ ከያዛቸው የጉንፋን በሽታ መዳን ወይም የህመሙን ተፅዕኖ መቀነስ ይችላሉ፡፡3. ሲጋራ ማጨስሲጋራ ማጨስ የጉንፋን በሽታን ያባብሳል፡፡በተለይም ተከታታይ እና የማያቋርጥ ሳል እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ጉንፋን የያዛቸው ሰዎች ሳንባቸው የሚቆጣ ሲሆን፥ በዚሁ ላይ ሲጋራ ሲጨመርበት ጉዳት ይደርስበታል፡፡ ይህ ደግሞ የጉንፋንን እድሜ ያራዝማል የህመሙንም ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፡፡የጤና ባለሙያዎቹ ጉንፋን የያዛቸው ሰዎች ምንም ቢሆን ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ እንዳለባቸው ጠቁመው፥ በተጨማሪም ሲጋራ ከሚያጨስ ሰው መራቅም መራቅ እንደሚኖርባቸው ይመክራሉ፡፡4. የሰውነት ድካምን አለማዳመጥጉንፋን በሰዎች ላይ ሲከሰት ሰውነት ይዝላል፤ የራስ ምታትም ሊከሰት ይችላል፡፡በዚህ ጊዜ በጉንፋን የተያዙ ሰዎች ሰውነታቸው የሚያሳያቸውን የድካም እና የመዛል ስሜት ወደ ጎን ማለት እንደሌለባቸው ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡በሰውነት ላይ የሚታዩት የድካም ስሜቶች የጉንፋኑን ደረጃ ስለሚጠቁሙ ትኩረት ሊሰጧቸው ግድ ነው፡፡እንቅልፍ ጥሩ መፍትሔም መሆኑ ተጠቁሟል፤ እረፍት ማድረግም ተገቢ ነው፡፡5. በሰውነት ውስጥ በቂ ውሃ እንዳይኖር ማድረግበዘልማድ ፈሳሽ ነገሮችን መጠቀም ጉንፋን ያባብሳል የሚሉ ሰዎች አይጠፉም፤ ሆኖም ህመም ሲያጋጥም በርካታ ፈሳሽ ነገሮችን መጠጣት ጥሩ ነው፡፡በሰውነት ውስጥ በቂ ውሃ መኖሩ፥ በአፍንጫ ውስጥ የሚገኙ ፈሳሾችን እርጠበታማነት በመጨመር ቫይረሱን እንዲያጥቡ እና እንዲያስወግዱ ያደርጋል፡፡6. ፀረ-ባክቴሪያ ወይም አንቲባዮቲክን አብዝቶ መጠቀም ጉንፋን በዋናነት በቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡በመሆኑም በሽታው በባክቴሪያ እስካልተከሰተ ድረስ አንቲ ባዮቲክ ወይም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡ብዙ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መጠቀም ደግሞ ሌሎች በሽታዎች ወደ ሰውነት ክፍል እንዲገቡ መፍቀድ ሲሆን፥ ባክቴሪያዎችም እንዲላመዱ በር ይከፍትላቸዋል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡በመሆኑም ጉንፋን ያመማቸው ሰዎች ፀረ ባክቴሪያን ባይጠቀሙ ይመከራል፤ በምትኩ ሌሎች የጉንፋን መድሃኒቶችን ሃኪምን በማማከር መውሰደም ጥሩ መፍትሔ ነው፡፡7. የበሽታ አምጪ ተህሶዋችን ማዛመት

ጉንፋን በሰውነት ውስጥ በተከሰተ በሁለት ወይም በሶስት ቀን ውስጥ ነው የህመም ምልክቶቹ የሚታዩት፡፡

ይህም መሆኑ የመተንፈሻ አካላትን ማለትም አፍ እና አፍንጫን በመሃረብ ለመሸፈን ያመቻል፡፡

ይህ ደግሞ ቫይረሱ የጉንፋን ታማሚዎች በሚያነጥሱበት ወቅት ሌሎች በሽታ አምጭ ተህዋስያን ወደ መተንፈሻ አካላላቸው እንዳይገቡ ይከላከላል፡፡

እንዲሁም በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይዛመት በአንጻራዊነት ያግዛል፡፡

እጅን ደጋግሞ መጣጠብም ጥሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ጉንፋን ወደ ቤተሰብ፣ ወደ ባልደረባ እና ሌሎችም ሰዎች እንዲተላለፍ፣ በሽታ አምጪ ተህዋስያን በሰውነት ውስጥ እንዲስፋፉ ስለሚያደርግ ጥንቃቄ ማድረግ ለሁሉም ጤና ጠቃሚ ነው፡፡

8. ለጉንፋን ህመም ዝቅተኛ ግምት መስጠት

ከጉንፋን ጋር በተያያዘ በሰዎች ዘንድ በአብዛኛው የሚሰራው ስህተትህመሙ ሲያጋጥም ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረግ ነው፡፡

የጉንፋን የህመም ምልክቶች ሲያጋጥሙ ትኩረት አለመስጠት በሽታው የከፋ ጉዳት እንዲያደርስ እድል ይፈጥራል፡፡

ነገር ግን ህመሙ እንደተከሰተ ወዲውያኑ ፈጣን ምላሽ መስጠት የጉንፋን እድሜን ያሳጥራል፡፡

 

 

http://www.newsmax.com

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy