Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጫማ አምራቾችን በስፋት ወደ ዓለም ገበያ እንዲገቡ የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ መሆን ጀመረ

0 1,094

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሀገር ውስጥ የጫማ አምራቾች ወደ አለም አቀፍ ገበያ በሰፊው መግባት የሚያስችላቸውን ፕሮጀክት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለፀ።˝ስሪተ ኢትዮጵያ˝ የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ፕሮጀክት ከአምስት ዓመት በኋላ ከኢትዮጵያውያን የሀገር ውስጥ ጫማ አምራቾች ብቻ የሚገኘውን ዓመታዊ ገቢ 250 ሚልየን ዶላር ለማድረስ ታቅዷል።ለዚህ ስራ ከተለዩ 10 ፋብሪካዎች ውስጥ በሰባቱ ስራውን ለመጀመር የሚያስችል የጥራት አስተዳደር ስርዓት ተግባረዊ የተደረገ ሲሆን፥ ሁለት ፋብሪካዎችም የሙከራ ትዕዛዝ ተቀብለዋል።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ወደ ውጪ ገበያ ከሚላኩ ጫማዎች የሚገኘው ገቢ እያደገ ቢመጣም በዚህ ውስጥ ሀገር በቀል አምራቾች ያላቸው ድርሻ አነስተኛ ነው።ይህንንም ድርሻ ለማሳደግ የስሪተ ኢትዮጵያ ፕሮጀከት የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም በማሳደግ እና ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲገቡ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy