የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የቀጣይ አስር ዓመታት የዓቅም ግንባታ ስትራቴጂና ግብ ተወያይቶ ለማጽደቅ መዘጋጀቱን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽሕፈትቤት አስታወቀ ፡፡
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በመቐለ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እየገመገመ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል ፡፡የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባው ባለፉት ስድስት ወራት በልማት፣በመልካም አስተዳደርና በጥልቅ ተሃድሶ ጉዳይ የስራ ክንውኖች እየገመገመ መሆኑን ነው ያመለከተው ፡፡