መንግሥት የአገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅና የሕዝብ ሠላም፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። ይህንን አዋጅ ተከትሎ በተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ እና አዋጁን ያረቀቁ ባለሙያዎች በአስረጅነት ተገኝተው ስለ አዋጁ ዝርዝር ገለጻም አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ወገኖች «በአዋጁ ምክንያት ብዙ ሰው እየታሰረ ነው፤ በትክክል ወንጀለኞች ናቸው የተባሉት በሙሉ ፍርድ ቤት አልቀረቡም፤ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ነው የሚገኙት። አዋጁ ጠቀሜታው ምን ድረስ ነው? ሰላምን ለማምጣትስ ምን ያህል አስተማማኝ ነው?» የሚሉ ጥያቄዎች ሲያነሱ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባይታወጅ ኖሮ በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ ብጥብጥና መንግሥትን እስከማናጋት ሊደርስ እንደሚችል አደገኛ ሁኔታ ይፈጠር እንደነበር ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህልውና ራሱ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችል እንደነበር ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ሥራውን በጀመረበት ወቅት ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቀሰቀሱት የሁከት እንቅስቃሴዎች በቡድን ወይም በግል የተሳተፉና የተለያዩ ወንጀሎችን የፈጸሙ በአዋጁ መሠረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ እጃቸውን እንዲሰጡና የዘረፉትንም ንብረት እንዲመልሱ በጥብቅ ማሳሰቢያ በመነገሩ፤ በዘረፋ ንብረት በማውደምና ህይወት በማጥፋት የተሳተፉ እጃቸውን ሲሰጡ፤ የጦር መሳሪያን ጨምሮ በርካታ የግልና የህዝብ ንብረቶችን የማስመለሱ ሥራም ተጠናክሮ ተሠርቷል። እንዲሁም የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ውስጥ ውስጡን ሲቀሰቅሱ የነበሩ፤ከትምህርት ገበታ ሆን ብለው በመቅረት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማደናቀፍ የሞከሩ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። ኮማንድ ፖስቱ በሁከቱ የተሳተፉትን ጉዳያቸውን እያጣራ በማስተማርና የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት እንዲለቀቁና ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ሲያደርግ፤ ከበድ ያለ ወንጀል የፈፀሙትን ደግሞ ለፍርድ የማቅረብ ተግባር አከናውኗል። የአዋጁን ውጤታማ አፈፃፀም ለመገምገም ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የፀጥታ አካላት ባካሄዱት ውይይት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የተሠራው ሥራ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን አስመልክቶ የመከላከያ ሚኒስትሩ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ሲራጅ ፈጌሳ መግለጻቸው ይታወሳል። በሂደትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋልን ጨምሮ የተወሰኑ ክልከላዎችን ያስቀረ መመሪያ በማውጣት የተወሰኑ ክልከላዎች እንዲቀሩ አድርጓል። አሁንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአገሪቷ ለውጥ እየታየ መምጣቱን ህብረተሰቡ በመገንዘቡ የአዋጁ የጊዜ ቆይታ እንዲራዘም ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ ሴክሬታሪያቱ ባካሄደው ጥናትና መረጃ የመሰብሰብ ሥራ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም እንደሚፈልግ ሲገለጽ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የአዋጁ መራዘም የሚወሰነው አዋጁን ባፀደቀው አካል በመሆኑ ትናንት በተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው ስብሰባ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬተሪያት እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለምክር ቤቱ የወጣውን አዋጅ ማራዘም ያስፈለገበትን ጉዳይ በማስረዳት፤ በአገሪቷ ከዚህ ቀደም ተከስቶ የነበረውን ብጥብጥ እና አለመረጋጋት በተደነገገው አዋጅ ለመቆጣጠር ቢቻልም በአንዳንድ ክልሎች መካከል አሁንም ድረስ ያለውን አለመግባባት ተገን በማድረግ ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት የሚፈልጉ ፀረ ሰላም ኃይሎች መኖራቸው ፤ ማህበረሰቡን ለብጥብጥ እና ሽብር የሚቀሰቅሱ ፅሑፎች መበተናቸው እንዳልቀረ፤ በህቡዕ ተደራጅተው የሚገኙ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ሙከራ የሚያደርጉ ኃይሎች እንዳልከሰሙ፤ በትጥቅ ትግል ተደራጅተው የነበሩ ኃይሎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዕርምጃ ማጥራት ቢቻልም አሁንም ድረስ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በመኖራቸው፤ ሰላም እና ፀጥታ ለማስከበር የሚንቀሳቀሱ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ፈንጂ በመወርወር እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላት እንዳሉ ገልጸው እነዚህን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ህብረተሰቡ የአዋጁን መራዘም «ይፈልገዋል ወይስ አይፈልገውም?» የሚል የዳሰሳ ጥናት በማድረግም የአዋጁ መራዘም አስፈላጊ እንደሆነ ሴክሬታሪያቱ በመረዳቱና ለምክር ቤቱ በማቅረቡ ምክር ቤቱ በአገሪቱ ፍፁም ሰላም ሰፍኖ ያላለቁ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ፤ የፀረ ሰላም ኃይሎች እኩይ እንቅስቃሴም እንዲገታ የአዋጁን የቆይታ ጊዜ ለአራት ወራት አራዝሟል። ለዘመናት በጦርነት ውስጥ ለኖረችና ከጦርነት ተላቅቃ በተሳካ የልማት ጎዳና እየተራመደች ላለች አገር ልማቷን የሚያፋጥን እንጂ ወደ ኋላ የሚጎትት ሁኔታ እንዲኖር የሚፈልግ ህብረተሰብ አይኖረንምና ለሰላም ሲባል የሚወሰደው ዕርምጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ – See more at: http://ethpress.gov.et/addiszemen/index.php/2015-04-26-07-42-33/item/11979-2017-03-31-18-19-07#sthash.sb8Ued5u.dpuf
- Comments
- Facebook Comments
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos