Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለጣና ሀይቅ የብዝሃ ሕይወት ስጋት የሆነው አረም እየተወገደ ነው

0 650

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለጣና ሀይቅ ብዝሃ ሕይወት ስጋት ከሆነው የእቦጭ አረም ውስጥ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ሁለት ሺህ ሔክታር የሚጠጋ መሬት ነጻ መደረጉን የሰሜን ጎንደር ዞን መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ዘመቻው ከተጀመረበት ከባለፉት አራት አመታት ጀምሮ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መንገድ በተካሄደ የተጠናከረ እንቅስቃሴም ሀይቁን ሸፍኖ የነበረ ከ36ሺ ሄክታር በላይ አረም መወገዱን ገልጿል።በመምሪያው የአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት ማረጋገጥ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሙሉ ስሉጥ ለኢዜአ እንደገለጹት አረሙ የሀይቁን ብዝሃ ህይወት ስጋት ላይ ከመጣል ባለፈ ማህበራዊ፣ አካባቢያዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች እያደረሰ ነው፡በተለይ የሀይቁ አዋሳኝ በሆኑት በጎንደር ዙሪያና በደንቢያ ወረዳዎች አረሙ የእርሻ መሬት በመውረር የሰብል ምርት እንዲቀንስ እያደረገ ይገኛል።የአካባቢውን የግጦሽ መሬት በመውረርም የአርሶ አደሩ የቤት እንስሳት የመኖ ሳር እጥረት እንዲገጥማቸው ከማድረጉም ባሻገር አረሙን የተመገቡ እንስሳትም ለጉዳት መጋለጣቸውንና የወተት ምርት ጥራትና መጠን ላይም ችግር ማስከተሉን ተናግረዋል።መምሪያው አረሙ የፈጠረውን ችግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም ለማስወገድ ባለፉት አራት አመታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ ባከሄደው ዘመቻ 36ሺ ሄክታር መሬት ከአረም ነጻ ማድረግ ተችሏል፡፡ዘንድሮም ሀይቁ በሚያዋስናቸው ወረዳዎች በሚገኙ 12 ቀበሌዎች በልማት ቡድኖች የተደራጁ ከ52ሺ በላይ ነዋሪዎችን በአረም ስራው በማሳተፍ ከ5ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን መጤ አረም ለማጽዳት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።ባለፉት ስድስት ወራትም የእምቦጭ አረሙን ከሀይቁ ዳርቻ ለማስወገድ በተደረገ ርብርብ በአረሙ የተወረረ 1ሺ 750 ሄክታር መሬት ከአረሙ ነጻ መድረጉን ጠቁመው ቀሪውን በያዝነው በጋ ለማከናወን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።”የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር በላይነህ አእምሮ በሀይቁ ላይ የተከሰተው እምቦጭ የተባለው አረም ጉዳቱ የከፋ ነው” ሲሉ ተናግዋል።”የእርሻና የከብቶቻችንን የግጦሽ መሬት በመውረር ችግር ላይ ጥሎናል፤ ላለፉት አራት ዓመታት ያደረግነው አረሙን የማስወገድ ስራ ተስፋ ቢኖረውም አረሙ የመራባት አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ ድካማችንን አክብዶታል” ብለዋል ።የምእራብ ደንቢያ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር አየልኝ መንግስቴ በበኩላቸው “አረሙ ሃይል አለው፤ በሰው ጉልበት ብቻ መቆጣጠር አይቻልም፤ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥረት ካልተደረገ በአርሶአደሩ ጉልበት ብቻ የሚደረገው ጥረት ከባድ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዘሩና በቁርጥራጩ አማካኝነት በፈጣን ሁኔታ የሚስፋፋውን የእምቦጭ አረም በስነ-ህይወታዊ ዘዴ ማስወገድ እንዲቻል የጎንደርና የባህርዳር ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ምርምር መጀመራቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy