Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለ600 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ተዘጋጅቻለሁ – የደቡብ ክልል

0 721

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የደቡብ ክልል በጥናት የተለዩ 600 ሺህ ስራ ፈላጊዎችን የስራ ባለቤት ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ አለ።የክልሉ ርዕስ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ የሚውል 3 ቢሊየን ብር መዘጋጀቱን ተናግረዋል።ርዕስ መስተዳደሩ በበጀት አመቱ ግማሽ አመት 250 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።

ስራ ከተፈጠራለቸው ወጣቶች መካከል 150 ሺህ ያህሉ ቋሚ ስራ ያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ በጊዜያዊነት ነው ወደ ስራ የገቡት።ለእነዚህ በስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ክልሉ ግማሽ ቢሊየን ብር በጅቶ ስራ ላይ ማዋሉን ርዕሰ መስተዳደሩ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅትም ለ600 ሺህ ወጣቶችን የስራ ባለቤት ለማደረግ ዝግጅት ተጀምሯል ያሉት አቶ ደሴ፥ የክልሉ መንግስት ወጣቶቹ ሊሰማሩባቸው የሚችሉ የስራ ዘርፎችን መለየቱን ገልፀዋል።

በገጠር በግብርና ማለትም በመስኖ፣ ገበያ ተኮር ምርት፣ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና እርባታ፣ የንብ ማነብ፣ የአነስተኛ የግብርና ምርት ማቀነባበር ዘርፎች ወጣቶቹ ቢሰማሩባቸው ውጤታማ ይሆናሉ ተብለው ታምኖባቸዋል።

በከተማ ደግሞ በኮንስትራክሽን ግብአት አቅርቦት፣ የእንጨትና የእንጨት ውጤቶች የብረት ምርትና አቅርቦት መመረጣቸውን ነው ርዕስ መስተዳደሩ የተናገሩት።ለዚህ ስራ ማከናወኛ የሚሆን የብድር አቅርቦት መዘጋጀቱንም አቶ ደሴ ገልፀዋል።በክልሉ ለወጣቶች ለምርት የሚሆን በገጠር ከ50 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በከተማም በተመሳሳይ የመሬት ልየታ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ወጣቶችን ማበቃት የሚችሉ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፥ በቀጣይ ለወጣቶቹ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በተያዘው አመት በተለዩት ዘርፎች እንዲሰማሩ የማደረግ ስራ ይከናወናል ተብሏል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy