Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምሪያ ምክትል ስራ አስኪያጅ በድጋሚ በቁጥጥር ስር ዋሉ

0 1,236

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምሪያ ምክትል ስራ አስኪያጅ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በድጋሚ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪው አቶ ፍቃዱ አሰፋ ካሁን ቀደም በተከሰሱበት ጉዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተለቀው የነበረ ቢሆንም፥ ዓቃቢ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በመሻሩ ዛሬ ዳግም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ ፍቃዱ እና የኤቢ ፕላስቲክ ማምረቻ ባለቤት አቶ አብርሃም ጌታቸው፥ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በተፈፀመ ግዢ ከ78 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

የአቃቢ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው አንደኛ ተከሳሽ አቶ ፍቃዱ አሰፋ በ2005 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ባወጣው የእቃ ግዢ ጨረታ ሙስና ሰርተዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሹ ለጋራ መኖሪያ ቤት የሳኒተሪ መገጣጠሚያ እቃ ግዢ ጨረታ ሲወጣ፥ ከሁለተኛ ተከሳሽና የኤቢ ፕላስቲክ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ጌታቸው ጋር በመመሳጠር ከደረጃ በታች የሆነ የመፀዳጃ እና ፍሳሽ ማስወገጃ ቁሳቁስ ከዋናው ጋር ተመሳስሎ እንዲቀርብ አድርገዋል የሚል ክስ ነው የቀረበባቸው።

በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ክሱ ዳግም የሚታይ ሲሆን፥ ተከሳሹ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሱን ይከታተላሉ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy