Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መረጃ ለዴሞክራሲ ግንባታ ንጹህ አየር ነው-የኢፌዴሪ ኮሙኒኬሽን ጉ/ ጽ/ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ

0 379

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መለያ የሆነውን የከተሞች መድረክ ኘሮግራም የከተማ ኗሪዎችና አመራሩን ፊት ለፊት በማገናኘት በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ እያደረገ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ ኘሮግራሙን የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚቻልበትን ግብዓት ለማግኘትና የእስካሁኑን አካሄድ ለመገምገም ያስችል ዘንድ ሃገር አቀፍ ሲምፖዚየም ዛሬ በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል፡፡በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ሚኒስቴር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንዳሉት መረጃ ለዴሞክራሲ ግንባታ ንጹህ አየር ነው፡፡የዴሞክራሲ ግንባታ በሚዲያ ይገነባል ፣ሲገነባም ህዝቡን መምሰል አለበት፡፡ሚዲያውም የህዝቡን ድምጽ መስማት አለበት፣ሀሳቡን የሚያንሸራሽር ማህበረሰብ ሲፈጠርም በዴሞክራሲያዊ ግንባታም ሀሳቡን መግለጽ ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ሀሳብ ማክበርም አለበት ብለዋል፡ዶክተር ነገሬ አክለውም ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማሳደግ ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡ሚዲያ ደግሞ ተሳትፎን ያሳድጋል፣ ነገር ግን ሚዲያዎች በየክልሎቻቸው ብቻ ስራቸውን ካደረጉ ለብሄራዊ መግባባት የሚፈጥሩት ፋይዳ እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም ፣ምንም አይፈይድም ይልቁንም እንደ ሀገር ሁላችንም የሚኖረን ነገር ሊኖረን ይገባል ነው ያሉት፡፡አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በዚህ ረገድ የተሻለ ይንቀሳቀሳል፡ሆኖም ከዚህ በላይ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለባቸው የሱፍ በበኩላቸው ሚዲያችን ህብረተሰቡ የሚናገርበት አንደበት ነው፡፡የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ በማሳየት መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡የህዝቦች የአስተሳሰብ ልዕልና ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡የከተሞች መድረክም የዚህ ነጸብራቅ ነው፡፡በመሆኑም ድርጅቱ ከተቋቋመበት አንጻር በቀጣይ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡በሲምፖዝየሙም በሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣የሚዲያ ተቋማት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የክልሉና የፌዴራል ባለስልጣናት ታድመውበታል፡፡
በመሠረት አስማረ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy