Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ውይይት ይደነቃል – የአውሮፓ ኅብረት

0 380

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መንግሥት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን ውይይት የአውሮፓ ኅብረት በአድናቆት እንደሚመለከተው የኅብረቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፌደሪካ ሞግኸሪኒ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአውሮፓ ኅብረቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፌደሪካ ሞግኸሪኒ ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነት ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

የኅብረቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፌደሪካ ሞግኸሪኒ እንደተናገሩት ኅብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ዙሪያ ሠፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።ኅብረቱ በሁሉም ዘርፎች በሚባል ደረጃ ከኢትዮጵያ ጋር አጋርነት እንዳለውና ይህንንም ይበልጥ ለማጠናከር ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በአገሪቱ ባለው የፖለቲካ ጉዳይ በጋራ ለመሥራት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ነው የተናገሩት።በመሆኑም በፖለቲካው መስክ መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ውይይት የሚበረታታና የሚደነቅ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህም በፖለቲካው መስክ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን አንስተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይም በዚህ ረገድ ለሚያደርጉት ጥረት ከጎናቸው እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከድርቁ ጋር በተያያዘ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የምትሰራውን ሥራ አድንቀዋል።

በዚህም ሳትወሰን በአፍሪካ ቀንድ አገራት ላለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ኢትዮጵያ የድርሻዋን በመወጣት ያበረከተችው አስተዋጽዖ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ተቀብላ በማስተናገድም እንደ አገር የተጣለባትን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣች መሆኑን ነው የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ሠፋ ያለ ውይይት ማድረጉን ገልጸውላቸዋል።

ከዚህም ጎን ለጎን አገሪቱ ባጋጠማት የጸጥታ ችግር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም የሰላም መሻሻል በመታየቱ በመመሪያዎቹ ላይ መሻሻል መደረጉን ተናግረዋል።ይሁንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮም በሰብዓዊ መብት ላይ ምንም አይነት ጥሰት አለመከሰቱን አስረድተዋል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት::

ለዚህም ደግሞ ከዓመት በፊት በኅብረቱና በኢትዮጵያ መካከል የተደረሰውን የስትራቴጂክ አጋርነት ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንደምትሰራ ጠቁመዋል።

በቀጣይ በቤልጂየም ርዕሰ-መዲና ብራሰልስ የሚካሄደው የቢዝነስ ፎረም ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ በማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበል እየሰራች ያለውን ሥራ እንደምታጠናክርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ካሳ ገብረዮሃንስ መናገራቸውን ኢዚአ ዘግቧል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy