Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መንግስት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

0 287

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢፌዴሪ መንግስት ከየትኛውም አጀንዳ በላይ በቆሻሻ መደርመስ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ከቆሻሻው በመለየት ሟቾች በክብር እንዲያርፉ ላደረጉት የአካባቢው ወጣቶች እና ነዋሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በዛሬው እለትም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡትን ሀዘንተኞች በስፍራው ተገኝተው አፅናንተዋል።

አቶ ደመቀ በተለይም አብዛኞቹ ሟቾቹ ሴቶች እና ህፃናት እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸው ሀዘኑን የበለጠ ልብ የሚሰብር አድርጎታል ብለዋል።

የሀዘኑ ተጋሪ የሆነው መንግስትም ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከየትኛውም ስራ እና አጀንደA በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመረባረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን በማፈላለጉ ረገድ ሰፊ ስራ ቢሰራም አሁንም የሚቀር እና የሚጠረጠር ካለ ስራው የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ርብርብ የፌዴራሉ መንግስት እንደሚያግዝም ተናግረዋል።መጋቢት 2 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የ113 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።በዚህም ከረቡዕ መጋቢት 6 እስከ መጋቢት 8 2009 የሶስት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን መታወጁ አይዘነጋም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy