Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሰሜን ኮሪያ አራት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

0 1,186

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሰሜን ኮሪያ አራት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ጃፓን አቅጣጫ ማስወንጨፏ ተነገረ።የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ምንጮች እንደገለፁት፥ ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር ከምትዋሰንበት አከባቢ የተወነጨፉት ሚሳኤሎች 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ “የጃፓን የኢኮኖሚ ዞን” ተብሎ በተከለለ አከባቢ ላይ ወድቀዋል።ባለፈው አርብ ሰሜን ኮሪያ በዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ እየተደረገ ላለው ወታደራዊ ልምምድ አፀፋ የሚሆን ሚሳኤል እንደምትተኩስ አስጠንቅቃ ነበር።ዛሬ ማለዳ ላይ የተተኮሱት ሚሳኤሎች ዓይነት በዝርዝር አለመታወቁ ነው የተገለፀው።ሆኖም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ ምንም ዓይነት ሚሳኤልም ሆነ የኑክሌር ሙከራ እንዳታደርግ ማእቀብ ጥሎባታል።ባለፈው የፈረንጆቹ ወር ፒዮንግያንግ አዲስ ዓይነት የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጋ እንደተሳካላት መግለጿ ይታወሳል። ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy