Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሰራዊታቸውን ወደ ሶማሊያ ለላኩ አገራት ድጋፍ እንዲደረግ የመንግስታቱ ድርጅት ጠየቀ

0 311

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አልሻባብ በሶማሊያ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ሰራዊታቸውን ወደ ሀገሪቱ ለላኩ የአፍሪካ አገራት ድጋፍ እንዲደረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠየቀ፡፡

አሚሶም በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና መረጋጋትን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት ዘላቂ ድጋፍ ያስፈልገዋል ያሉት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉታሬዝ ናቸው፡፡አሚሶም ከሚጠበቅበው በታች በቁሳቁስ የተደራጀ ነው ያሉት ጉታሬዝ በዚህ ውስጥም ቢሆን ግን ውጤታማ ስራ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ጅቡቲና ብሩንዲ የተወጣጡ 22 ሺህ ወታደሮች በአሚሶም ጥላ ስር ሶማሊያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡የአውሮፓ ህብረት አሚሶምን ለመደገፍ ቀዳሚ ሲሆን፤ በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ለዚሁ ስራ ወጪ ቢያደርግም ድጋፉን በ20 በመቶ ቀንሶታል፡፡እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ በሶማሊያ የተሰማራው የአሚሶም ጦር አልሻባብን ከሞቃዲሾና ከሌሎች ዋና ዋና ከተሞች አስለቅቋል፡፡ምንጭ- ኤቢሲ ኒውስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy