Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሰጋቱራ በመቀላቀል ያዘጋጀውን እንጀራ ሲያከፋፍል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

0 642

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ ሰጋቱራ በመቀላቀል ያዘጋጀውን እንጀራ ለተለያዩ ሆቴሎች እና የእንጀራ አከፋፋዮች ሲያከፋፍል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 መነን አካባቢ አዝመራው እንጀራ አከፋፋይ የሚል ድርጅት ከፍቶ ሲሰራ የነበረ ነው።ግለሰቡ በስሩ ከቀጠራቸው ሰባት ሰራተኞች ጋር በመሆን፥ በየቀኑ እስከ ስድስት በርሜል የሚሆን ከሰጋቱራ ጋር የተቀላቀለ ሊጥን በመጋገር ለ12 ሆቴሎች እና እንጀራ አከፋፋዮች ሲያከፋፍል ቆይቷል።

የክፍለ ከተማው የምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ክብካቤ አስተዳደር ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስራት ሙሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አሰሪው ከአንዱ ሰራተኛው ጋር በክፍያ ምክንያት በመጠላታቸው ሰራተኛው ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ምክንያት ሊያዝ ችሏል።
ፖሊስ በቦታው ላይ ሲደርስም 16 ኩንታል ከሰጋቱራ ጋር የተቀላቀለ ዱቄት እና ሊጋገር የተዘጋጀና ወደ ሶስት ኩንታል የሚገመት ሊጥ በቦታው ተይዟል።

police_car.jpg

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለውና የተቀላቀለው ዱቄትከዱቄቱ በተጨማሪ ለመጋገር የተዘጋጀ ሊጥም ተይዞ ለናሙና ወደ ፓስተር የተወሰደ ሲሆን ቀሪው እንዲወገድ ተደርጓል ነው ያሉት።አሰሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውልም የጠቆመውን ሰራተኛውን አስያዝከኝ በሚል በፖሊሶች ፊት በጥፊ እንደመታው ነው የተገለጸው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy