NEWS

ሰጋቱራ በመቀላቀል ያዘጋጀውን እንጀራ ሲያከፋፍል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Admin

March 24, 2017

በአዲስ አበባ ከተማ ሰጋቱራ በመቀላቀል ያዘጋጀውን እንጀራ ለተለያዩ ሆቴሎች እና የእንጀራ አከፋፋዮች ሲያከፋፍል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 መነን አካባቢ አዝመራው እንጀራ አከፋፋይ የሚል ድርጅት ከፍቶ ሲሰራ የነበረ ነው።ግለሰቡ በስሩ ከቀጠራቸው ሰባት ሰራተኞች ጋር በመሆን፥ በየቀኑ እስከ ስድስት በርሜል የሚሆን ከሰጋቱራ ጋር የተቀላቀለ ሊጥን በመጋገር ለ12 ሆቴሎች እና እንጀራ አከፋፋዮች ሲያከፋፍል ቆይቷል።

የክፍለ ከተማው የምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ክብካቤ አስተዳደር ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስራት ሙሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አሰሪው ከአንዱ ሰራተኛው ጋር በክፍያ ምክንያት በመጠላታቸው ሰራተኛው ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ምክንያት ሊያዝ ችሏል። ፖሊስ በቦታው ላይ ሲደርስም 16 ኩንታል ከሰጋቱራ ጋር የተቀላቀለ ዱቄት እና ሊጋገር የተዘጋጀና ወደ ሶስት ኩንታል የሚገመት ሊጥ በቦታው ተይዟል።

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለውና የተቀላቀለው ዱቄትከዱቄቱ በተጨማሪ ለመጋገር የተዘጋጀ ሊጥም ተይዞ ለናሙና ወደ ፓስተር የተወሰደ ሲሆን ቀሪው እንዲወገድ ተደርጓል ነው ያሉት።አሰሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውልም የጠቆመውን ሰራተኛውን አስያዝከኝ በሚል በፖሊሶች ፊት በጥፊ እንደመታው ነው የተገለጸው።