Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲን እና ቤተሰቦቻቸው በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

0 1,964

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲን እና ቤተሰቦቻቸው በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉየሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያዎች እና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀ መንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን እና ቤተሰቦቻቸው በአዲስ አበባ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉንም የደርባ ሲሚንቶ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሌ አሰግዴ በዛሬው እለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።ዛሬ የተደረገው ድጋፍ አደጋው ከደረሰ በኋላ ኮሚቴ ተቋቁሞ ድጋፍ እንዲደረግ በታዘዘው መሰረት የተደረገ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።ይህን መሰሉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው፥ ሚድሮክ በቀጣይም ተጎጅዎች መልሰው አስከሚቋቋሙ ድረስ ድጋፉን ያደርጋል ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy