Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሙስና ወንጀል ተከሶ የተሰወረው ግለሰብ በቴሌቪዥን በመታየቱ በቁጥጥር ስር ዋለ

0 768

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሙስና ወንጀል ተከሶ የተሰወረው ግለሰብ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ሚኒስቴር የአስተዳደር ጉዳይ ዳኛ በመሆን በአገልግሎት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በስልጠና አገልግሎት ላይ እያለ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ተከትሎ ነው።

ተከሳሽ አቶ ታሪኩ ወንድምአገኝ በ2007 ዓ.ም የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፥ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ አቃቢ ህግ ሆኖ ሲሰራ፥ በዳኛ በኩል ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ከባለጉዳይ 10 ሺህ ብር መቀበሉ በመረጋገጡ በወቅቱ ክስ ተመስርቶበታል።

ክሱ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት ተከፍቶ ምስክር የቀረበበትና የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርብ ታዞ የመከላከያ ምስክር በማሰማት ላይ እያለ ነበር የተሰወረው።

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ችሎትም፥ ግለሰቡ በሌለበት በ2 አመት ከ3 ወር እስራትና በ1 ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

ፖሊስም ከተሰወረበት ጊዜ ጀምሮ የማፈላለግ ስራ ሲያከናውን ቆይቶ ባለፈው ሳምንት የስልጠና አገልግሎት እየሰጠ በቴሌቪዥን መስኮት ታይቷል።

በዚህም በድሬዳዋና በአዲስ አበባ ፖሊስ ጥምረት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ተከሳሽ በቀጣይ ድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ሆኖ የተላለፈበትን የእስር ቅጣት ይቀበላል።

መረጃውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አድርሶናል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy