Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በምስራቅ ሸዋ ዞን 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተያዙ

0 1,245

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ከትክክለኛ የብር ኖቶች ጋር ቀላቅሎ ሲገበያይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባልደረባ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት ግለሰቡ ትናንት የተያዘው በሳምንት አንድ ቀን በሚውለው የአለም ጤና ከተማ ገበያ ላይ ነው።ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ከትክክለኛው የብር ኖቶች ጋር በመቀላቀል ብዙ ኩንታል ጤፍ እየሸመተ በነበረበት ወቅት ሕብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ነው።ግለሰቡ በወቅቱ 41 ባለ መቶና አራት ባለ ሃምሳ ሀሰተኛ የብር ኖቶች ከበርካታ ትክክለኛ የብር ኖቶች ጋር ቀላቅሎ ይዞ ነበር።እንደምክትል ኮማንደር አስቻለው ገለጻ ግለሰቡ በሞጆ ከተማ በንግድ ሥራ የተሰማራ ሲሆን፥ ሀሰተኛ የብር ኖቶቹን ከየትና እንዴት እንዳመጣቸው ለማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።ወቅቱ ምርት ተሰብስቦ ለገበያ የሚቀርብበት በመሆኑ ሕብረተሰቡ በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ እንዲያደርግና ሲያጋጥመውም ለፖሊስ ወዲያው እንዲያሳውቅ አሳስበዋል። ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy