Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሶስት የማቋቋሚያ ደንቦች ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች አሳለፈ

0 424

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ25ኛው መደበኛው ስብሰባው ሶስት የማቋቋሚያ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ወጣቶች የልማትና የለውጥ ስትራቴጂ፣ በሴቶች የልማትና የለውጥ ስትራቴጂ እና በሳይበር ታለንት ልማት ኢንስቲትዮት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡በዚህም ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በስፋት ከተወያየ በሃላ በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲን ለማስፈፀም በሚረዱ ፓኬጆች ባለፉት ዓመታት ወጣቱን ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታች ስራዎች መከናወኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ወጣቶች የገጠር፣ የከተማና የአርብቶ አደር፣ ከፊል አርብቶ አደር ፓኬጆችን በመከለስና በማሻሻል ወጣቶችን ይበልጥ ተጠቃሚና ተሳታፊ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የወጣቶች የልማትና የእድገት ስትራቴጂን አጽድቋል፡፡

በተመሳሳይ ሴቶች በተለይ በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጎልበት እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ የሴቶች የልማትና የለውጥ ስትራቴጂ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

በዚህም ምክር ቤቱ በቀረበው ስትራቴጂ ላይ ማሻሻዎችን በማከል ታትሞ ወደ ስራ እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ብሏል መግለጫው፡፡በመጨረሻም የሳይበር ታለንት ልማት ኢንስቲትዮት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ከተወያየ በሃላ ማሻሻያዎች በማከል ደንቡ ፀድቋል፡፡

በሳይበር ምህዳሩ ውስጥ ሀገሪቷ ቁልፍ ሚና እንድትጫወት ለማስቻል ደረጃውን የጠበቀ መደበኛ ትምህርት መስጠት የኢንስቲትዮቱ ዓላማ መሆኑን በመግለጫው ተብራርቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy