CURRENT

በቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ከነገ ጀምሮ ጸሎተ-ፍትሐት ይደረጋል

By Admin

March 15, 2017

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቆሼ በተሰኘው አካባቢ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ከነገ ጀምሮ ጸሎተ-ፍትሐት እንደሚደረግ ገለጸች።

ቤተክርስቲያኗ በአደጋው ለተጎዱና መጠለያ ላጡ ወገኖች የሚውል የ200 ሺህ ብር እርዳታ እንዲሰጥ መወሰኗንም አስታውቃለች።ቤተክርስቲያኗ በአዲስ አበባ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም ምሽት ዜጎች ላይ በደረሰው የሞተ አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገልፃለች። “በደረሰው ሕልፈተ ሕይወት ለተጎዱ ቤተሰቦች እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትና ብርታትን እንዲሰጥ፤ የሟቾችንም ነፍስ በመንግስቱ እንዲቀበል ፀሎት ይደረጋል” ስትልም በመግለጫው አመልክታለች። ምንጭ፦ ኢዜአ