Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ 76 ሚሊየን ብር ደርሷል

0 468

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ 76 ሚሊየን ብር ደርሷል።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አድማሱ ጸጋዬ፥ ዩኒቨርሲቲው በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ሚሊየን ብር፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 600 ሺህ ብር እንዲሁም ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከ650 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።በአጠቃላይም በዛሬው እለት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን የተቀበሉት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ድሪባ ኩማ፥ አስተዳደሩ የተደረገው ድጋፍ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም እንዲውል በአደራ ሃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በአይነት የሚደረገው ድጋፍ፥ ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ እንደደረሰ ከአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy