Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በቆሼ የደረሰውን አደጋ መንስኤ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁሟል፤ የሟቾቹ ቁጥርም 113 ደርሷል

0 385

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲሰ አበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዳሜ እለት በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 113 መድረሱ ተገለጸ።የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፥ ፍለጋው ወደ መጠናቀቅ ደርሷል፤ በፍለጋው የአካባቢው ህብረተስብ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል ብለዋል።

በተለይም የአካባቢው ወጣቶች በፍለጋው ወቅት ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ ነው ያሉት ከንቲባው፤ የአካባቢው ህብረተሰብ እና ለወጣቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ከንቲባው አያይዘውም፥ የአደጋው መንስኤ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ባለሙያዎች እንደሚጣራ አስታውቃል።

መንስኤውን ለማጥናትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከአሜሪካው ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን አስታውቀዋል።አስከሬናቸው የተገኘ ማቾች ስርዓተ ቀብር በዛሬው እለትም መፈፀሙን ገልፀዋል።

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቆሻሻ ክምር መደርመስ ጉዳት የደረሰባቸውንና በአደጋ ስጋት ከቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዛሬው እለት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ቤተሰቦቻቸውን በአደጋው በሞት አጥተው በድንኳን ውስጥ ሀዘን የተቀመጡት ሰዎች ከንቲባው ጉብኝታዋል፡፡ከንቲባው የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ምን አይነት ድጋፍ እየተደረገ እንዳለ እና እየተሰጠ ስላለው ድጋፍ ተመልክተዋል።

በአደጋው ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን በሞት የተነጠቁ ሰዎች ከከንቲባ ድሪባ እጅ ከከተማ አስተዳደሩ ወጪ የተደረገ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለዋል።

የተደረገው የገንዘብ ድጋፍም በአንድ ህይወቱ ባለፈ ሰው ለቀብር ማስፈፀሚያ ተብሎ የ10 ሺህ ብር የተሰጠ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም ለ11 ሰዎች የገንዘብ ድጋፉ ተሰጥቷል።የሚደረገው የቀብር ማስፈፀሚያ የገንዘብ ድጋፍ በቀጣይ የሟቾች ቤተሰቦችን በማጣራት እንደሚሰጥም ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ ተመሳሳይ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል በሚል ስጋት ከቤታቸው ተፈናቅለው በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ አንድ ወጣት ማእከል ለገቡ ዜጎችም ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።ሆኖም ግን እተደረገ ያለው ድጋፍ ትክክለኛውን ሰው ጋር እደረሰ አይደለም በማለት በርካቶች አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

እንዲህ አይነት ችግሮችን ለመቅረፍ እና በትክክል መረዳት ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት በክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ የሚመራ የተቋቋመ ኮሚቴ መኖሩን እና ድጋፉን የሚያስተባባር አካል መቋቋሙ ተመልክቷል፡፡ከተማ አስተዳደሩ ከሚያደርገው ድጋፍ ባለፈም በግለሰቦች በማህበራት እና በአካባቢው ነዋሪዎች ጭምር ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።

ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎችም ከተማ አስተዳደሩ በዘላቂነት የምንቋቋምበት መንገድ ሊያዘጋጅልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።ከንቲባ ድሪባ ኩማም፥ መጠለያ በማዘጋጀት እና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራ ተናግረዋል።በዛሬው እለትም በፍርስራሹ ስር የቀሩ አስክሬኖችን የማፈላለግ እና የማውጣት ስራም እንደቀጠለ ነው።በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ስፍራው ድረስ በመሄድ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እና በማጽናናት ላይ ይገኛሉ። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy