Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በቻይና ፓርላማ 100 ቢሊየነር አባላት ይገኛሉ

0 941

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቻይና ፓርላማ 100 ቢሊየነር አባላት እንዳሉት አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡

በቻይና ዓመታዊ የህግ አውጪወች እና አማካሪዎች ስብሰባ በቤጅንግ በተከፈተበት ወቅት አንድ ሪፖርት ከፖላንድ ወይም ከስዊድን ዓመታዊ ምርት እኩል ሃብት ያላቸው 100 ቢሊየነሮች በቻይና ፓርላማ ውስጥ አባል መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

ቻይና የላይኛው እና የታችኛው በሚባሉ ምክር ቤቶቿ 5 ሺህ 129 ኣባላት አሏት፡፡

በሻንጋይ መሰረቱን ያደረገው ሑሩን የተሰኘ ሪፖርት 209 ያህሉ አባላት 507 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አላቸው ሲል ይፋ አድርጓል፡፡

ሺ ጂን ፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት የፈረንጆች 2013 ጀምሮ ሙስናን በመዋጋት ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩትን ቻናውያን ህይወት የሚለውጥ ስራ ሰርተዋል፡፡

የቻይናውያን ህዝቦች ተወካዮች ወይም የፓርላማ አባላት የሃብት መጠን በየጊዜው እየጨመረ መሄድ ፕሬዚዳንት ሺን እያስተቻቸው ነው፡፡

በአራት ዓመት ውስጥ እንኳ ቢሊየነር የፓርላማ አባላቱ 64 በመቶ የሀብት እድገት አስመዝግበዋል፡፡

መቀመጫውን በሻንጋይ ያደረገው ሁሩን ይፋ እንዳደረገው የላይኛው እና የታችኛው የምክር ቤት አባላት ከሀገሪቱ እድገት በላይ የሃብት መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡

ከሁለቱም ምክር ቤቶች ውስጥ 209 የሚሆኑ አባላት እያንዳንዳቸው 2 ቢሊየን ዩዋን ወይም 209 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሃብት እንዳላቸው ነው ሪፖርቱ የዘረዘረው፡፡

እነዚህ አባላት ሀብታቸው ሲደመር 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዩዋን ወይም 507 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል፤ ይህም ከቤልጂየም ዓመታዊ የምርት መጠን ጋር እኩል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ሃብት ያላቸው ሲሆን እንደ ሁሩን ሪፖርት 100 የሚሆኑት ቢሊየነር የፓርላማ አባላት በፈረንጆች 2013 አመት 1 ነጥብ 84 ትሪሊየን ዩዋን ሀብት ነበራቸው፡፡

በዚህ ዓመት ግን አጠቃላይ ሃብታቸው 3 ትሪሊየን ዩዋን ደርሷል- ጭማሪውም 64 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ከ2013 እስከ 2016 ባለው ተመሳሳይ ጊዜ ሀገሪቱ በየዓመቱ የ7 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ስታስመዘግብ የፓርላማ አባላቱ ሀብት ደግሞ 13 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

የፓርላማ አባላቱ ባለፀጋ መሆን በገዥው የኮሙኒስት ፓርቲ የታቀደ እና ታማኝ የፓርላማ አባላትን በማምጣት የተሻለ የመንግስት አሰራርን ለማስፈን ታስቦ መሆኑንም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

የኢኮኖሚ ጉዳይ ተንታኞች ደግሞ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር ያደርጋል ሲሉም ያጣጥሉታል፡፡

ምንጭ፡- http://fortune.com

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy