Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአማራ ክልል ለህዳሴው ግድብ ግንባታ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከ1 ቢሊዮን 25 ሚሊዮን ብር በላይ ደርሷል

0 334

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአማራ ክልል ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከ1 ቢሊየን 25 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡

በክልሉ የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት ስድስተኛው ዓመት  በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው ።በክልሉ የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎና ድጋፍ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳው ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የክልሉ ህዝብ ድጋፉን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

እስካሁንም  በቦንድ ግዥ እና በስጦታ የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ   ከ1 ቢሊየን 25 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡በተጓዳኝም የግድቡን ዘላቂነት ለማረጋገጥ በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች 18 ቢሊየን ብር የሚገመት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ ማከናወናቸውንም ጠቅሰዋል።

የክልሉ ምሁራንና የኪነጥበብ ባለሙያዎችም ህዝቡ ለግድቡ ያለውን አስተሳሰብ ወደ አንድ በማምጣትና አለም አቀፍ ጫናዎችን በመቀነስ ረገድ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አቶ ጌትነት ጠቁመዋል ።

የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት ስድስተኛ ዓመት በዓል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በፓናል ውይይት፣ በጥያቄና መልስ ውድድር፣ በስፖርታዊ ውድድሮችና በሌሎችም ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የፊታችን አርብ በሙሉዓለም የባህል ቡድን፣ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲና በፌደራል የግድቡ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ትብብር በግድቡ ግንባታ ዙሪያ የተዘጋጀ ሙዚቃዊ ቲያትር የምረቃ ስነ ስርዓት እንደሚካሄድም ተመልክቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy