Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአየር ትራንስፖርት የሚገለገሉ መንገደኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ የሚያስመዘግቡበት አሰራር ተተገበረ

0 1,011

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአየር ትራንስፖርትን ተጠቅመው ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሀገር ውስጥ እንደገቡ የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ የሚያስመዘግቡበት አሰራራር መተግበሩን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ገለፀ።

ከዚህ ቀደም መንገደኞች 24 ሰዓት እስካልሞላቸው ድረስ የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ እንዲያስመግቡ አለመገደዳቸው፥ ሀብትን እና የውጭ ምንዛሪን ለማሸሽ መንገድ መፍጠሩን የጠቀሰው ባለስልጣኑ አዲሱ አሰራር ተግባራዊ በተደረገ ጥቂት ወራት ውስጥ አዝማሚያው ቀንሷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ፥ የአየር ትራንስፖርትን ተጠቅሞ ሀገር ውስጥ የሚገባ የየትኛውም ሀገር መንገደኛ ከ24 ሰዓት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቆየ ይዞት የገባውን ገንዘብ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንዳለበት ይጠቅሳል።

ይህ ማለት በመመሪያው መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ በአየር ትራንስፖርት ተጠቅመው 24 ሰዓት ሳይሞላቸው ሀገሪቱን እንደ ሌላ መጓጓዣ ተጠቅመው ትራንዚት የሚያደርጉ ሰዎች፥ የያዙትን ገንዘብም ሆነ ጌጣ ጌጥ እንዲያሳውቁ አይጠበቅባቸውም ማለት ነው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት አዋጅ ማንኛውም ተጓዥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲገባ የያዘውን ገንዘብ እና ጌጣጌጥ 24 ሰዓት ሳይጠብቅ ማሳወቅ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ የመንገደኞች ጓዝ ጉዳይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ በየነ እንደሚሉት፥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትራንዚት ከሚያደርጉ መንገደኞች መካከል ሳያሳውቁ ገንዘብ ይዘው ከሀገር ለመውጣት የሚያልሙት ቁጥራቸው ጨምሯል፡፡

ገንዘቡን ይዘው ስለመግባታቸው አለማሳወቃቸው አደጋ መሆኑ የተለየ ሲሆን፥ በተለይ በ2008 ዓ.ም አዝማሚያው ጎልቶ ታይቷል።

በ2008 ዓ.ም ብቻ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ዜጋ በሆኑ መንገደኞች ሊወጣ ሲል መያዙን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፥ ከዚህ ውስጥ በክርክር ሂደት የተመለሰ፣ ጉዳዩ እየታየ ያለ እና ጉምሩክ የወረሰው መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያውያን መንገደኞች በ100 ሺህዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር ይዘው ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል።

በመመሪያው ላይ የነበረው የህግ ክፍተት በ24 ሰዓት ውስጥ ሀብትን ለማሸሽ፣ የውጭ ምንዛሪን ከሀገር ለማስወጣት መንገድ ከፍቷል።

ከማላዊ በተነሳ መንገደኛ ስድስት ኪሎ ግራም ያልተዘጋጀ ወርቅ ሲንቀሳቀስ የተያዘ ሲሆን፥ ብዙ ቁጥር ያላቸው ጌጣጌጦች በተመሳሳይ ሁኔታ ሊዘዋወሩ ሲሉ ተይዘዋል ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ።

ይህ ሁሉ ችግር የተፈጠረው ደግሞ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት አዋጅ ማንኛውም ተጓዥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገባ ከ24 ሰዓት በፊት በማንኛውም ጊዜ የያዘውን ገንዘብ እና ጌጣጌጥ ማሳወቅ እንዳለበት እየደነገገ መሆኑ የህግ መጣረስን ያሳያል፡፡

አሁን ላይ አዋጁን የበላይ በማድረግ የተከሰቱ አደጋዎችን ለማስቀረት ማንኛውም ተጓዥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገባ የያዘውን ገንዘብና ጌጣጌጥ እንዲያሳውቅ ግዴታ መቀመጡን አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት፥ አሰራሩ ተግባራዊ ከተደረገ ከጥቂት ወራት ወዲህ ትራንዚትን ተጠቅመው ገንዘብን ለማስወጣት የሚሞክሩ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል፡፡ FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy