CURRENT

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Admin

March 12, 2017

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ የተከሰተው ትላንት ምሽት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ አደጋው በመኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰ በመሆኑ ለሰው ህይወትና ንበረት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከአደጋው የተረፉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሙሉ ንብረቶቻቸውና የሰው ህይወት ጉዳትና መጥፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው እንዳሉት በአደጋው ምክንያት እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው 37 ሰዎች በአለርት ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡ የአይን እማኞች ለኢቢሲ እንደተናገሩት ግን ከአደጋው ከባድነት አንፃር የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ ይችላል፡፡