NEWS

በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 72 ደረሰ

By Admin

March 14, 2017

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካቢ በደረሰው የመደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳስታወቀው አደጋው በደረሰበት ስፍራ እያካሄደ ባለው የነፍስ አድን ስራ እስከ ትላንት ምሽት ድረስ የሟቾች ቁጥር 65 ደሶ ነበር፡፡አሁንም አደጋው በደረሰበት ቦታ እየተደረገ ያው ጥረት መቀጠሉን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያለክታል፡፡በትላንትናው ዕለት በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች የቀብር ስነ ስርዓት በየ እምነት ተቋማቸው መፈፀሙንና ሌሎች ደግሞ ቤተሰቦቻቸው ወዳሉበት አካባቢ አስክሬናቸው መሸኘቱ ይታወሳል፡፡