Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በድርቁ ሳቢያ በቆራ ሀይሌ ዞን እስካሁን ከ 40 ሺህ በላይ የቁም እንስሳት ሞተዋል

0 2,784

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ድርቅ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በቆራ ሀይሌ ዞን እስካሁን ከ 40 ሺህ በላይ የቁም እንስሳት ለሞት ተዳርገዋል።በዞኑ ድርቁ እያስከተለ ያለውን ችግር ለመመከት መንግስት 14 ውሃን መሰረት ያደረጉ ማዕከላትን አቋቁሞ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እና እንክብካቤ እያደረገ ይገኛል።

የድርቁ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ከዚህ ስለሚከፋ እየተሰጠ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ድርቁን ተከትሎ በተወሰኑ አካባቢዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተ ሲሆን፥ 18 ጊዜያዊ የማከሚያ ቦታዎችን በማዘጋጀት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ተደርጓል።

አቶ አህመድ ያሲን አሊ የዞኑ ዋና እስተዳዳርተወካይ በበኩላቸው በዞኑ ድርቁ ላስከተለው ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከክልሎችና ከፌደራል መንግስት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይቋረጥ የተማሪዎች ምገባ በትምህርት ቤቶች እየተካሄደ መሆኑን ነው አቶ አህመድ ያነሱት፡፡በዞኑ ያሉ እንስሳት እንዳይጎዱ ድርቅ ካልተከሰተባቸው የክልሉ ዞኖች መኖ እና ውሃ እንዲቀርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ተወካዩ፡፡ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ውሃን መሰረት ባደረገ መልኩ አርብቶ አደሮችን የማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተጋልጠዋል።

 

 

 

 

በአላዛር ታደለ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy