Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅራቢያ የደረቅ ወደቦች ግንባታ ሊካሄድ ነው

0 358

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢንዱስትሪ የሚመርቱ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጪ ለመላክ እንዲቻል በኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅራቢያ የደረቅ ወደቦች ግንባታ ሥራና የማስፋፋት ተግባር እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ።

የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ገብረሕይወት እንደተናገሩት፥ አሁን ያሉትን ሰባት የደረቅ ወደቦች ከማስፋፋት ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢም ደረቅ ወደቦች ይገነባሉ።

እንደ አቶ ደሳለኝ ገለጻ በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ የደረቅ ወደብ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፥ በአማራ ክልል በወረታ ከተማም ሌላ የደረቅ ወደብ ለመገንባት የጥናት ሥራ እየተካሄደ ይገኛል።

የደረቅ ወደቦች ግንባታ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚወጡ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጪ ለመላክ እንደሚያስችሉ ምክትል ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ወደ ውጪ የሚወጡ ዕቃዎችን በጥራትና በአነስተኛ ወጪ የሚላኩበትን መንገድ ለማመቻቸት ተጨማሪ የደረቅ ወደብ ማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የድርጅቱ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ተፈራ በበኩላቸው፥ ከውጪ ወደ ሃገር ውስጥ ከሚገቡ ኮንቴነሮች መካከል 80 በመቶውን የሚይዘው የሞጆ የደረቅ ወደብ ተርሚናል ነው።

ለዚህ ተርሚናል የበለጠ አቅም ለመፍጠር በሚያስችል መልኩም የማስፋፊያ ስራ እየተከናወነለት ይገኛል ብለዋል።

የደረቅ ወደቡ ማስፋፊያ የሚከናወነው አሁን ካለው የ60 ሄክታር መሬት ስፋት ወደ 140 ሄክታር ለማድረስ መሆኑንም ነው አቶ መስፍን ያስረዱት።

ከጂቡቲ የሚጫኑ ኮንቴነሮችን በባቡር በማጓጓዝ ለማራገፍ የሚያስችል በስድስት ሄክታር ላይ ያረፈ የባቡር ሐዲድ ግንባታም እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ለሚራገፉ ዕቃዎች ማቆያ የሚሆኑ ሁለት ትላልቅ መጋዘኖች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሁለት ተጨማሪ መጋዘኖች እንደሚገነቡ ነው የገለጹት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy