በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻዕብያ ወታደሮች መካከል ውግያ ተቀሰቀሰ። ውግያው የተቀሰቀሰው መረብ-ለኸ/ራማ/ ወረዳ ተሻግሮ ክሳድ ዒቃ በሚባል ስፍራ በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻብያ ወታደሮች መካከል ሲሆን በውግያው ኮነሬል ኣባዲ ገብረ መዓሾ/ወዲ ገብሩ/ የተባለ የጦር መሪን ጨምሮ 58 የሻዕብያ ወታደሮች መገደላቸው ታውቋል። ውግያው እስከ አሁን መቀጠሉንም የመረብ ለኸ ወረዳ ፀጥታ ፅቤት አስታውቋል።