Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በካምፓላ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አገኘች

0 1,381

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኡጋንዳ ካምፓላ እየተካሄደ ባለው 42ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ  አገኘች።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ስታስገኝ፤ አትሌት ሀዊ ፈይሳ የብር ሜዳሊያ አምጥታለች፤ ኬንያ የነሐስ ሜዳሊያ ወስዳለች።

በወንዶች ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኡጋንዳ ወርቅ፣ ኢትዮጵያ ብር፣ ኬንያ ነሐስ አግኝተዋል፤ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ ነው ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው።

በድብልቅ የዱላ ቅብብል ውድድርም ኢትዮጵያ የብር፣ ቱርክ የነሐስ ሜዳሊያ ሲያገኙ ኬንያ የወርቅ ሜዳሊያው ባለቤት ሆናለች።

የአዋቂ ሴቶችና ወንዶች ዛሬ የሚጠበቁ ውድድሮች ናቸው።

ኢትዮጵያ 29 አትሌቶችን ጨምሮ 43 የልዑካን ቡድን አባላትን ወደ ካምፓላ መላኳ ይታወቃል።

ውድድሩን በአንደኝነት የሚያጠናቅቁ አትሌቶች 30 ሺህ፣ ሁለተኛ የሚሆኑት 15 ሺህ፣ ሶስተኞቹ ደግሞ የ10 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

የቡድን አንደኞች 20 ሺህ፣ ሁለተኞች 16 ሺህ እንዲሁም በሶስተኝነት የሚያጠናቅቁ 12 ሺህ ዶላር ያገኛሉ።

ኢትዮጵያ እስካሁን በተሳተፈችባቸው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮናዎች 96 የወርቅ፣ 101 የብርና 58 የነሐስ በድምሩ 255 ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። ENA

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy