Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጋምቤላ ክልል ድንበር ዘለል የወንጀል ድርጊቶችን የመከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው–አቶ ጋትሉዋክ ቱት

0 278

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በጋምቤላ ክልል ድንበር ዘለል የወንጀል ድርጊቶችን በመከላከል የህብረተሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ገለጹ።

ለአንድ ወር ያክል የሰለጠኑ ከአንድ ሺህ 200 የሚበልጡ የክልሉ የሚሊሻ አባላት ተመርቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰልጣኝ የሚሊሻ አባላቱ የሥራ መመሪያ ሲሰጡ እንደገለጹት መንግስት የክልሉን ህብረተሰብ ሰላም ለማስጠበቅ የጸጥታ መዋቅሩን እያጠናከረ ይገኛል።

በአኝዋሃና ኑዌር ዞኖች በድንበር ዘለል የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የሚደርሰውን ጥቃት በዘላቂነት ለመከላከል የክልሉና የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር በዋና ዋና መግቢያ በሮች ላይ ለማጠናከር የሚያግዙ የመሰረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“እነዚህን ታጣቂዎች በዘላቂነት ለመከላከል በጠረፋማ ቀበሌዎች ከአንድ ሺህ 200 በላይ የአካባቢ ሚሊሻዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደረጓል” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የጥበቃ ኃይል በመመደቡም ነዋሪዎች ተረጋግተው የዘወትር ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸው የኡቡዋ ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አግዋ ኝጌዎ በሰጡት አስተያየት ልጆች ከአካባቢያቸው በታጣቂዎቹ እንደሚወሰዱና ድንገተኛ ጥቃትም ይደርስባቸው እንደነበረ አስረድተዋል።

”ቀደም ሲል እንደ አሁኑ በየቀበሌው የሚሊሻ አደረጃጀት ቢፈጠር  ኖሮ የሚሞትም ሆነ የሚወሰድ ህፃን አይኖርም ነበር” ያሉት ወይዘሮ አግዋ መንግስት ሚሊሻዎችን አደራጅቶ በመመደቡ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በተደረገ ጥረት ድንበር እየተሻገሩ በሚመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚደርሰውን ጥፋት ማቃለልና ስጋቱንም ማስወገድ የሚቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ አችዋ ኡቦንግ ናቸው።

በተለያዩ አጋጣሚዎች የተወሰዱ እና ያልተመለሱ ቀሪ ህጻናትና ንብረቶችም እንደሚመለሱ ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር ከተዘጋጁት የሚሊሻ አባላት መካከል አቶ ኡቦንግ ኦቡያ በሰጡት አስተያየት እንደ አሁኑ ቢደራጁ ኑሮ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ያጋጥማቸው የነበረው የጸጥታ ችግር እንደማይፈጠር ገልጸዋል።

ርዕሰ-መስተዳደሩ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በተለያየ ጊዜ የጸጥታ ችግር የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ጎብኝተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy