NEWS

በ7 ሚሊየን ብር የተገነባው የአየር ብክለት መመርመሪያ ማዕከል አገልግሎት ጀመረ

By Admin

March 23, 2017

በ7 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው 3ኛው የአየር ብክለት መመርመሪያ ማዕከል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ማዕከሉ ከአየር ብክለት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በመመዝገብ ለፖሊሲ አውጪዎችና ፈፃሚ ባለሙያዎች መረጃን በማቅረብ፥ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል አቅም ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ማዕከሉ ሀዋሳ ላይ የተገነባው ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ልማት እና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመኖሩ ነው፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንዳሉት፥ በየጊዜው ከሚመጣው የአየር ትንበያ መረጃዎች ጋር እራሱን አዛምዶ የሚንቀሳቀስ ህብረተሰብ ለመገንባት በትኩረት መሰራት ይገባል፡፡

ባለፉት ዓመታት ሀገሪቷ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብም የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ምርትና ምርታማነት ላይ ጫና እያሳደረ ነው ያሉት አቶ ፈጠነ፥ ይህንን ጉዳት ለመከላከል የሜትሮሎጂ ትንበያን አስቀድሞ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ኤጀንሲው በዛሬው እለት አለም አቀፉን የሜትሮሎጂ ቀን በሀዋሳ እያከበረ ነው፡፡