Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ብዝሃነት በህብረ-ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት

0 1,704

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

(በእውነቱ ብላታ – ሚኒስትር ዲኤታ)
የህብረ-ብሄራዊነት ዋነኛ መገለጫዎች ከሆኑ አበይት ጉዳዮች የብሄር፤ የቋንቋ፤ የሀይማኖት እና የባህል ብዝሃነትግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ብዝሃነት በህብረ-ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት ውስጥ በሂደት የግድ መፈጠርየሚገባው ነው፡፡ ብዝሃነት ልዩነቶችን በሚያስተናገድ ሥርዓት ውስጥ ከህብረ-ብሄራዊ ውበትነት አልፎ የስርዓቱዋልታና ማገር እንዲሁም ምሰሶ ሆኖ በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት ያጠናክራል፡፡
ብዝሃነት በተሻለ ደረጃ ግልጽነትን ስለሚፈጥር የኪራይ ሰብሳቢነት፤ የጠባብነትና የትምክህት እንዲሁም የፀረ ሰላምኃይሎችን መደበቂያ ዋሻ ለመናድ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ የዘርፋ ጠቢባን ብዝሃነትከባድና አድካሚ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሂደት ውስጥ ታልፎ የሚገኝ ወይም የሚደረስ መሆኑን ለማስረዳት ሲሉኅብረ ብሄራዊነትን እንደ ድፍድፍ ነዳጅ ሲገልጹት ብዝሃነትን ደግሞ እንደ ተጣራ ነዳጅ እና እንደነጠረ ወርቅወይም ውድ ማዕድን ይመስሉታል፡፡ ብዝሃነትን የሚያስተናግድ የአመለካከት የበላይነት ባልሰፈነበት ወቅትምህብረ-ብሄራዊነትን በህግና በመመሪያ ደረጃ መተግበር የሚቻል ሲሆን ብዝሃነት ግን የህብረ-ብሄራዊነትንየአመለካከት ልዕልና ማረጋገጥን ይጠይቃል፡፡
ሀገራችን ብዙሃነትን ማስፈንና ማክበር ይቅርና በተፈጥሮ ብቻ በውስጧ ያለውን ልዩነት እንኳን ማስተናገድ ተስኗትነበር፡፡ ህብረ-ብሄራዊት የሆነችው ሀገራችን በውስጧ ያሉትን ልዩነቶች አምና መቀበል ተስኗት ለበርካታ አስርትዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥና የኋልዮሽ ጉዞ ሽምጥ ስትጋልብ ኖራ ለመናድ ጥቂት እርምጃ ሲቀራትብረ-ብሄራዊነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበለችው በሽግግሩ ዘመን ቻርተር፤ ኋላም በ1987 በኢፌዴሪ ህገ መንግስት ነው፡፡
ሀገራችን ልዩነቶችን አምና ለመቀበል ረጅም ዘመናትና መራራ ትግል ቢጠይቃትም አሁን ግን ከዚያ ሁሉ አስከፊየጨለማ ዘመን አልፋ ብዙህነትን በተግባር ለማረጋገጥ ረጅሙን ጉዞ በቁርጠኝነት ጀምራለች፡፡ የብዙህነት መረጋገጥእንደ እኛ ላለ ህብረ ብሄራዊ ሀገር የሰላም፤ የልማትና የዴሞክራሲ ማስፈኛ ወሳኝ መሰረት ስለሆነ በሚገባ አውቀንየበኩላችንን ድርሻ የመወጣት ሀላፊነት አለብን፡፡
በሀገራችን ብዙህነትን እውን ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች በህብረ ብሄራዊ የፈዴራል ስርዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ፤ መግባባት እና የአመለካከት የበላይነት በሁሉም ደረጃ ማረጋገጥ ይገኝበታል፡፡ በህብረ-ብሄራዊ የፌዴራልስርዓታችን ውስጥ በተፈጥሮ ያለው ልዩነት በሥራና በሂደት ወደ ብዙህነት ሲያድግ፤ ህብረ ብሄራዊነታችንበተግባር፤ በሥራ ሲረጋገጥ ሀገራዊ ውበታችንና ኩራታችን ይሆናል፡፡ ለብዙህነት መሰረት በሆነው የፌዴራልሥርዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ ሳይኖር የሚሰራ ስራ ለአንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ግንባታ፤ ለሰላም፤ለዴሞክራሲና ልማት የሚኖረው በጎ አስተዋፅዎ ባይኖርም አላስፈላጊ የገንዘብ፤ የጊዜ፣ የዕውቀትና የጉልበት ብክነትማስከተሉ አይቀርም፡፡ ስለ ብዝሃነት መስረታዊ መነሻና መድረሻ በአግባቡ መረዳትና ማስረዳት ሚና ወሳኝ ነው::
በመጀመሪያ ደረጃ ብዙህነት ማለት በተፈጥሮ የሚገኝ በዓይነት ወይም በልዩነት ላይ የተመሰረተ የቁጥር ብዙነትብቻ ሳይሆን ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን በልዩነቶቻችን ውስጥ ያለውን አንድነት የውበትና የጥንካሬ ምንጭለማድረግና ለማጎልበት በቁርጠኝነት በመስራት የሚረጋገጥ የጥምረት እና የጥረት ውጤት የሆነ ህብር ነው፡፡ብዙህነት የሚሠራበትና በአብሮነት ሂደት ልናሳካውና ልናጎለብተው የምንችል የመስተጋብር ውጤት ነው፡፡ ብዙህነት ማለት በሀይማኖቶችና ተቋሞቻቸው እንዲሁም በብሄር፣ ብሄረሰሰቦች ወይም ህዝቦች መካከል ሊኖርየሚገባውን ግንኙነት በመቻቻል፤ በመከባበርና በመረዳዳት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ህብረት እንዲሆን ለማድረግበሚፈጠረው መልካም ግንኙነት የሚረጋገጥ የአብሮነት ውጤት ነው፡፡ ብዙህነት እንደ ልዩነት በተፈጥሮ ብቻየሚገኝ ሳይሆን በተጨባጭ እንዲኖርና አንዲረጋገጥ ለማድረግ ስራን እና ጥረትን የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህምአኳኋን ሲገነባ በህብረ ብሄራዊ ስርዓት ውስጥ ያለው ልዩነት የውበትና የአብሮነት ማሳያ/መገለጫ ይሆናል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ስንመለከት ብዙህነት ማለት መቻቻል ማለት ብቻ ሳይሆን ልዩነቶቻችንን በፈጠሩት እሴቶች እናለልዩነታችን መኖር ምክንያት በሆኑ ማንነቶቻችን ላይ መግባባት እና የጋራ ግንዛቤ (መረዳዳትን) መፍጠር ነው፡፡መቻቻል ለአብሮነት የሚያስፈልግ የጋራ እሴት ቢሆንም ተቻችሎ ለመኖር ግን አንዱ የሌላውን እምነት ምንነት እናማንነት በጥልቀት ማወቅ አስገዳጅ አይደለም፡፡ የማንነት እና የሀይማኖት ጥንቅሯ ብዙ በሆነባት አለማችን ውስጥመቻቻል ብቻውን ቁንፅል የሆነ እና ጨለምተኝነትንና ቅድመ-ቅኝት (Stereotypes) ለማስወገድም በራሱብቻውን በቂ አይደለም፡፡ በተለያዩ ማንነቶች እንዲሁም ሀይማኖቶች መሀል ሊወገድ የሚገባው ጨለምተኝነትእስካለ እና እስካልተወገደ ድረስ ጊዜያትን ቆጥሮም ቢሆን በአሉታዊነቱ ዋጋ የሚያስከፍል እዳ ሊሆን ይችላል፡፡ጨለምተኝነት ደግሞ መወገድ የሚችለውና የሚገባው ባማሩ ቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር በተረጋገጠ ቁርጠኝነትእና የስራ ውጤት ወይም መስዋዕት ነው፡፡
በሦስተኛ ደረጃ ብዙህነት ማለት በተለያዩ ሁኔታዎች በአጋጣሚ የሚፈጠር አንፃራዊነት (relativism) እናእንደየሁኔታው የሚለያይ/የሚቀያየር ሳይሆን በማንኛውም ሁኔታ እንዲኖር ለማድረግ የግድ ዋጋ ወይም መስዋዕትየሚከፈልለት/የሚከፈልበት ነው፡፡ ብዙህነት ዋጋ የሚከፈልለት እንደመሆኑ መጠን በአሁኑ ወቅት ብዙህነትንአስመልክቶ ያለ የአቅጣጫ ምልከታና እርምጃ የማንነት መገለጫዎቻችንን እንድንተው የሚጠይቅ አይደለም፡፡ ይህማለት ለአብሮነታችን ሲባል በሀይማኖቶች፣ በብሄር፣ ብሄረሰሰቦች፣ ህዝቦች ወይም ማንነቶች መሀል ያሉልዩነቶቻችንን መተው ወይም መካድ ሳያስፈልግ የጋራ በሆኑ ጉዳዮቻችን ላይ ግንኙነቶችን በመፍጠርና በማጠናከርአንድነትንም ጭምር ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡
በመጨረሻም ብዙህነትን የውይይት፤ የድርድር እንዲሁም የሰጥቶ መቀበል ባህል መጎልበት ውጤት ሆኖእናገኘዋለን፡፡ ብዙህነት ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ያደረገ ድርድርን፤ የጋራ መረዳዳትን እና ግንዛቤ የሚፈልግ ሂደት(ሥርዓት) ነው፡፡ ውይይት የተሳታፊዎች ሁሉ መስማማት ማለት ሳይሆን ለውይይቱና ድርድሩ መሳካት ከመነሻውአንስቶ የሚደረግን ቅን እና ፅኑ ፍላጐትን ጨምሮ መልካም የሆኑ የመወያያ ሃሳቦችን እንዲሁም ጥሩ ንግግርንየሚያስተናግድ ነው፡፡ይህንንም ለማሳካት ሁለት ነገሮችን መረዳት ይፈልጋል፡፡ በአንደኛ ደረጃ ልዩነታችንን አክብረን በአንድነት ለመኖርየሚጠቅሙን አስተሳሰቦችንና ግንኙነቶችን ማዳበር አለብን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዕለት ተዕለት ህይወታችንውስጥ አንዱ ከሌላው ጋር የሚጋራቸው መደበኛ ያልሆኑ መግባቢያዎች ጭምር ህብረ ብሄራዊነትን የሚያከብሩናየሚያንፀባርቁ መሆን ይገባቸዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy