Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ተራማጅ የዜጎች ንቅናቄ” አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው

0 289

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቀድሞው የፓርላማ አባልና የ”አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ” ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ሰይፉና አጋሮቻቸው፣በወጣት ምሁራን የተደራጀ “ተራማጅ የዜጎች ንቅናቄ” የተባለ አዲስ ፓርቲ ሊመሰርቱ ነው፡፡
ፓርቲውን የሚያደራጅ አካል ተቋቁሞ በመላ ሀገሪቱ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስፈልገውን የ1500 ሰዎች ፊርማ እያሰባሰበ መሆኑን ለአዲስ አድማስ የገለፁት አቶ ግርማ ሰይፉ፤በቀድሞ “አንድነት” ውስጥ በከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ ወደ ፖለቲካው ገብተው የማያውቁ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ወጣቶች በአዲሱ ፓርቲ ውስጥ መካተታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የቀድሞ “አንድነት” ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር መነሻ ምክንያቶች በሚገባ አጢነናል ያሉት አቶ ግርማ፤ በአዲሱ ፓርቲ ውስጥ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ በአባላት ምልመላ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄና ፍተሻ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡ ግለሰቦች የፓርቲው አባል የሚሆኑት አቋማቸው በሚገባ ተፈትሾ እንጂ አባል መሆን የፈለገ ሁሉ በዘፈቀደ እንዲቀላቀል አይደረግም ሲሉም አክለዋል – የቀድሞው የፓርላማ አባል፡፡
የፓርቲው ስያሜ “ተራማጅ የዜጎች ንቅናቄ” የተባለበትን ምክንያት ሲገልጹም፤ሃይማኖት፣ ፆታና ብሄር የማይለይ በመሆኑ ነው ብለዋል – አቶ ግርማ፡፡
ፓርቲውን ለማቋቋም የሚያስፈልገው የ1500 ሰዎች የድጋፍ ፊርማ ተሰባስቦ እንደተጠናቀቀም፣የፓርቲው መስራች ጉባኤ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy