Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 2ዐ ሺህ 659 ተለቀዋል፡- ቦርዱ

0 387

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከኦሮሚያ፣ ከአማራና ከደቡብ ክልሎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 2ዐ ሺህ 659 ተሃድሶ ወስደው እንዲለቀቁ ተደርገዋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 2ዐኛ መደበኛ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድን የክትትልና ቁጥጥር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት አዳምጧል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ስም ዝርዝር  እንዲታረሙ በተደረገበት ማዕከል ተለይቶ በክልል መስተዳድሮች አማካኝነት በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ እንዲታወቅ በመደረጉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ እንዲያውቁ ማስቻሉን የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርዶፋ ተናግረዋል፡፡

ቦርዱ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ድረስ 174 አቤቱታዎችን አስተያየቶችን የተቀበለ ሲሆን 54 የሚሆኑትን ጥቆማዎች ክትትልና ቁጥጥር ተደርጎባቸው አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት መተላለፋቸውን አቶ ታደሰ ወርዶፋ ተናግረዋል፡፡

12ዐ አቤቱታዎችንና ጥቆማዎችን ደግሞ ቦርዱ ለክትትልና ቁጥጥር ስራው  በግብአትነት ተጠቅሞባቸዋል ብለዋል፡፡

የክትትልና ቁጥጥር ስራ በየደረጃው ካለው ኮማንድ ፖስት፣ በናሙና ከተመረጡ ተጠርጣሪ  የተሃድሶ ሰልጣኞች ጋር በመወያየት መፈፀሙን እንዲሁም በግኝቶች ላይ ከየማዕከላቱ ኮማንድ ፖስት ሀላፊዎች ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር መከናወኑም  ተገልጿል፡፡

ቦርዱ በአጠቃለይ በሁለት ዙር የክትትልና ቁጥጥር ስራ ማከናወኑን የገለፁት አቶ ታደሰ ከኦሮሚያ፣ ከአማራና ከደቡብ ክልሎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 2ዐ ሺህ 659 ተሃድሶ ወስደው እንዲለቀቁ ተደርገዋል ብለዋል፡፡

457 ተጠርጣሪዎች በዕድሜና በጤና ምክንያት ምክር ተሰጥቷቸው የተለቀቁ ሲሆን 4 ሺህ 996 ተጠርጣሪዎች ደግሞ ጉዳያቸው በህግ ሂደት እየታየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች በሚያዙበትና በምርመራ ወቅት ከህግ ውጭ የሆነ አሰራር በተካተሉ አካላት ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንም አቶ ታደሰ ወርዶፋ ገልፀዋል፡፡

ቦርዱ በመጀመያው ዙር የክትትልና ቁጥጥር ሂደት የለያቸውን ችግሮች ለመፍታት ኮማንድ ፖስቱ መንቀሳቀሱንም ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉትን ዜጎች ሰብአዊ መብት ለመጠበቅና ሰላምን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ቦርዱ መመልከት መቻሉንም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy