የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዓመታዊ ወታደራዊ በጀቱ በ10 በመቶ እንዲያድግ እቅድ አቅርበዋል፡፡የትራም አስተዳደር የበርካታ ተቋማትን በጀት የሚቀንስበትን ሰነድ ዛሬ ምሽት ለአሜሪካ ኮንግረስ ያቀርባል፡፡
ትራምፕ ዓመታዊ የወታደራዊ በጀቱም በ10 በመቶ ለማሳደግ አልመዋል፡፡ለወታደራዊ ሥራዎች የሚውለው በጀትም 54 በሊየን ዶላር ጭማሪ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ለመከላከያ ኃይሉ ተጨማሪ ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶችን እና የባህር መርከቦች ለማቅረብ ማለማቸው የወታደራዊ በጀቱ ጭማሪ እንዲያሳ አድርገዋል፡፡ፕሬዚዳንቱ በበጀት እቅዳቸው የአካባቢ ጥበቃ ተቋምን ጨምሮ የበርካታ መስሪያ ቤቶች በጀት ለመቀነስ ማሰባቸውም ተነግሯል፡፡
ለዲፕሎማሲና ለውጭ እርዳታዎች የሚውሉ ወጪዎችም በበጀት ቅነሳው የተካተቱ ሲሆን እንደ አልጀዚራ ዘገባ 28 በመቶ የበጀት ቅነሳ እንደተደረገባቸው በእቅዱ ተጠቁሟል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለድንበርና የፀጥታ ጥበቃ ሥራዎች የሚሆን 312 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ በጀት ያቀዱ ሲሆን፥ 500 የድንበር ጠባቂዎችን እና 1 ሺህ የስደተኞች ጉዳይ ሰራተኞችን ለመቅጠርም አቅደዋል ተብሏል፡፡በበጀት ማዕቀፉ ውስጥ ለ2 ሚሊየን ሰዎች የህግ አገልግሎት የሚሰጠው ኮርፖሬሽን በጀት ይቀነስበታል ነው የጠባለው፡፡
የሰራተኞች ጉዳይ ቢሮ ስራ አጥ ዜጎችን ስራ እንዲያገኙ የሚያስችል ተቋም ሆኖ ሳለ 434 ሚሊየን ዶላር በጀቱ ቅነሳ ተደርጎበት በእቅዳቸው ውስጥ መካተቱ ተጠቅሷል፡፡ትራምፕ የበጀት እቅዳቸውን ዛሬ ምሽት ለኮንግረሱ አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው
ምንጭ፡- ሲኤንኤን እና ፕሬስ ቲቪ