English

ቻይና የአፍሪካን የኢንዱስትሪና ግብርና ዘርፎች ለማዘመን ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

By Admin

March 10, 2017

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ቻይና የአፍሪካ ሀገራት የኢንዱስትሪ እና የግብርና ዘርፎች እድገት እንዲፋጠኑ እና ዘመናዊ እንዲሆኑ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡

ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት መሪዎች 60 ቢለየን የአሜሪካ ዶላር በአህጉሪቱ መዋዕለንዋይ ለማፍሰስ በገባችው ቃል መሰረት ግማሽ ያህሉን ተግባራዊ ያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ለአህጉሩ ሀገራት ከገባቸው የገንዘብ መጠን እሰካሁን ገሚሱን በኢንዱስትሪ እና መሰረተ ልማት ግንባታዎች ዘርፎች ልማት እንዳዋለች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ቻይና በአፍሪካ ሞባሳ ናይሮቢ የባቡር መስመር ግንባታ እና በሂደት ላይ ያለው የታንዛኒያ ወደብ ግንባታ ለአህጉሪቱ እያደረገች ካለችው ድጋፎች መካከል ከፊሎቹ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የቻይና ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የነበረውን የካፒታል መጠን ወደ 10 ቢለየን የአሜሪካ ዶላር አሳድጓል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ዴይሊ ኒውስ