English

ናሳ በርካታ ሶፍትዌሮችን በነፃ አቀረበ

By Admin

March 04, 2017

ናሳ ቴክኖሎጂን በማስተላላፍ እና በማስፋፋት መርሃ ግብሩ በርካታ ሶፍትዌሮችን በነፃ ማቅረቡ ተሰምቷል።ናሳ በድረ ገጹ ላይ በነጻ ያቀረባቸውን ሶፍትዌሮችም የኩባንያው የ2017 ፣ 2018 ሶፍትዌር ካታሎግ መሆኑም ተነግሯል።ሶፍትዌሮቹንም ማንኛውም ሰው በነጻ በማውረድ መጠቀም እንደሚችልም ታውቋል።ናሳ ሶፍትዌሮችን በነፃ ማቅረብ የጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2014 ሲሆን፥ አሁን ላይ በርካታ ሶፍትዌሮችን ሲያቀርብም ይህ ለሶስተኛ ጊዜው ነው ተብሏል።ሶፍትዌሮቹም በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ ፎርማት ነው የቀረቡት።እንደ ናሳ ገለጻ፥ በነጻ የቀረቡት ሶፍትዌሮቹ ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ የፈጠራ ስራን ለሚሰሩ፤ ለአነስተኛ የንግድ ስራዎች፣ ለኢንዱስትሪዎች እና ለትምህርት አገልግሎት ያግዛሉ።ሶፍትዌሮቹ ስራን ለመፍጠር፣ የሰው ህይወት ለማዳን እና ገቢን ለመሰብሰብ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ናሳ አስታውቋል።ናሳ በነፃ ካቀረባቸው ሶፍትዌሮች ውስጥ የተወሰኑት፦

ናሳ በነፃ ያቀረባቸውን ሶፍትዌሮች እንዴት ማግኘት ይቻላል…?ሶፍትዌሮቹን ሙሉ በሙሉ ለመመልከት ይህን ይጫኑ፥ list of tools released by NASA.

ናሳ በነጻ ያቀረባቸውን ሶፍዌሮች ለማውረድ (download) ለማድረግ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፥ Download

ምንጭ፦ https://fossbytes.com