CURRENT

አሜሪካ ላፕቶፕ የጫኑ አውሮፕላኖች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ከለከለች

By Admin

March 21, 2017

አሜሪካ ከስምንት የመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ሀገራት የሚነሱ አውሮፕላኖች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ጭነው ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገደች፡ ክልከላው ላፕቶፕ፣ ታብሌቶች፣ ካሜራ፣ ዲቪዲ እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡የሞባይል ስልክ በክልከላው አልተካተተም፡፡የአሜሪካ የደህንነት ተቋም እንዳስታወቀው ክልከላው ያስፈለገው በመሳሪዎቹ የቦንብ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ በመሆኑ ነው፡፡ለምሳሌነትም አይ ኤስ እና አልሻባብ በላፕቶፕ የፈፀሟቸውን ፍንዳታዎች አቅርበዋል፡፡በክልከላው ከአፍሪካ የግብፅ እና ሞሮኮ አየር መንገዶች፣ ከአረብ ሀገራት ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ ቱርክ፣ ኳታር እና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ይገኙበታል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡