CURRENT

አምባሳደር ታዬ አጽቀ-ስላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለግብጹ ፕሬዚዳንት አቀረቡ

By Admin

March 28, 2017

በግብጽ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አጽቀ-ስላሴ ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ  የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ በግብጽ የኢትዮጵያ  አምባሳደር ታዬ አጽቀ-ስላሴ ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በቤተ-መንግስታቸው በመገኘት የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በስነ-ስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ ትሻለች።

የአምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ መሾምም በሁለቱ አገራት መካከል ላለው ግንኙነት መዳበር አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አክለዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት እንዳለ በማውሳት በስራ ቆይታቸው ወቅት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማዳበር እንደሚሰሩ ለፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል።

የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከተጀመረ ከ80 ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን አገራቱ በጋራ ጥቅም ላይ ባተኮሩ የንግድ፣የህዝብ ለህዝብ፣ፖለቲካና ማህበራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ  እየሰሩ ይገኛሉ።