CURRENT

አዲሱ የአሜሪካ የጤና ማዕቀፍ ፖሊሲ ዛሬ ድምፅ ይሰጥበታል

By Admin

March 24, 2017

በስራ ላይ የነበረውን የኦባማ የጤና መድህን ፖሊሲ ይተካል የተባለው አዲሱ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የጤና  ፖሊሲ ዛሬ በአሜሪካ ኮንግረስ ክርክር ተደርጎ ድምፅ ሊሰጥበት ቀን ተቆርጦለታል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ አገሪቱ በኦባማ  የጤና አገልግሎት ፖሊሲ ምክንያት አላስፈላጊ ወጪ ታወጣለች በሚል የበጀት ቅነሳ ሀሳብ ይዘው መቅረባቸውን ተከትሎ ነው አዲሱ የአሜሪካ የጤና ፖሊሲ ዛሬ ለክርክር የሚቀርበው፡፡

ይሁንእንጂ  አሁን የቀረበው አማራጭ የጤና ፖሊሲም ቢሆን ከሪፐብሊካኑ ጎራ ሳይቀር ነባሩን የጤና መድህን አገልግሎት በተሟላ ቁመና ሊተካ የሚችል አይደለም በሚል ከወዲሁ ተቃውሞ  ገጥሞታል፡፡

በፕሬዝዳንት ኦባማ የስልጣን ዘመን የተቀረፀው የጤና ፖሊሲ 20 ሚሊዮን አሜሪካዊያንን የጤና መድህን ዋስትና የተረጋገጠላቸው ሲሆን በአሁኑ እቅድ ግን እ.አ.አ በ2026 24 ሚሊዮን አሜሪካዊያንን ከጤና መድህን ሽፋን ውጭ የሚያግ ነው፡፡ ምንጭ ፡‑ ቢቢሲ