Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ የክልሉን ‹‹የኢኮኖሚ አብዮት››

0 455

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

– ኦዳ ትራንስፖርት ኩባንያን በ1.6 ቢሊዮን ብር ሊያቋቁም ነው  – ኬኞ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ አክሲዮን በሚያዝያ ይፋ ይደረጋልአዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት›› በሚል መርህ የሚደረጉ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር በይፋ አስታወቀ፡፡የክልሉ መንግሥት ይኼንን የኢኮኖሚ አብዮት በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የኦሮሞ ባለሀብቶች ጥምረት ምክር ቤት መሥርቷል፡፡በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ ዓላማው የኦሮሞ ሕዝብን መሠረት ያደረገ ቢሆንም ግቡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡‹‹የኦሮሞ ወጣቶችና አርሶ አደሮች እየተመዘገበ ካለው ዕድገት ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ማፋጠን፣ ሕዝባችንን በማንቃትና በማደራጀት ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ ለኢኮኖሚ ጥቅም አውሎ ከድህነት እንዲላቀቅ ማድረግ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የክልሉ ካቢኔ የመንግሥትና የባለሀብቱ ጥምረት ምክር ቤት የሚመራበትን ሕግና ስትራቴጂ ማፅደቁንም አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡ይኼንንም ተከትሎ አጠቃላይ ካፒታሉ 1.6 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን የሚገመት ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ለመመሥረት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል፡፡የክልሉ መንግሥት ለዚህ አክሲዮን ማኀበር መመሥረቻ 500 ሚሊዮን ብር የመደበ መሆኑን፣ በመጪው መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀሪውን ካፒታል ለመሰብሰብ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡በአክሲዮን ሽያጭ ከሚገኘው በተጨማሪ ከባንክ ብድር እንደሚገኝ አቶ አዲሱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ይህንን የአክሲዮን ሽያጭና የኩባንያውን ምሥረታ እንዲያስተባብሩ ከኦሮሞ ባለሀብቶች የኢሊሌ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ፣ አቶ ሲሳይ ዮሐንስ፣ አቶ አህመድ መሀመድ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አበራ ደሬሳ (ዶ/ር) መመረጣቸውን አቶ አዲሱ አክለዋል፡፡በክልሉ መንግሥት በኩል የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የከተማ መሬት አስተዳደር ኃላፊው አቶ ምትኩ ደሬሳ፣ የኦሮሚያ ደን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲዳ ድሪባ ተመድበዋል፡፡በሌላ በኩል ‹‹ኬኛ ቤቬሬጅ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ለመመሥረትም እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ አዲሱ አስረድተዋል፡፡ ይኼ ኩባንያ ከኦሮሞ ገብስ አምራች ገበሬዎች ጋር የእሴት ትስስር በመፍጠር ከብቅልና ከአልኮል ነፃ የሆኑ ‹‹የማልት›› መጠጦችን፣ የማዕድን ውኃ፣ የለስላሳ መጠጦች፣ ጭማቂዎች፣ የጠርሙስ ፋብሪካ፣ እንዲሁም የፕላስቲክና የፓኬጂንግ ዘርፎች ላይ የሚሰማራ መሆኑን አቶ አዲሱ አስረድተዋል፡፡የኬኛ ቤቨሬጅ ምሥረታና አክሲዮን ሽያጭ ሚያዝያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ እንደሚሆን አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡የእዚህን ኩባንያ ምሥረታ የሚመራ ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን፣ ሰብሳቢው የኦሮሚያ የከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡በአባልነት አቶ መሰለ ኃይሌ (የኤምኤች ኢንጂነሪንግ ባለቤት)፣ አቶ አካሉ ገለታ፣ ዶ/ር ሀሰን የሱፍ፣ አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል (የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ)፣ አቶ ሮቤል ሰዒድ፣ አቶ ፀሐይ ሽፈራው (የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት) መመረጣቸውን ገልጸዋል፡፡በቀጣይነትም የኦሮሞ ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማኅበርና አምቦ ፕመር የተባለ የማዕድንና የግብርና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማኅበራት እንደሚመሠረቱ አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በቅርቡ ከኦሕዴድ ወጣት ሊግ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ማቀጣጠል ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አስታውቀው ነበር፡፡‹‹በኢኮኖሚ ያልዳበረ ማኅበረሰብ ተላላኪ ነው፡፡ ቁጥር ብቻ ነው፡፡ የትም መድረስ አይችልም፡፡ ገንዘብ ያለው ወይም ሀብት ያለው፣ በኢኮኖሚ ጠንካራ የሆነው ወደ ፈለገበት ይነዳዋል፡፡ ስለዚህ መሥራት ነው ያለብን፡፡ የዓለምን ጥሩ የፖለቲካ ርዕዮት ብናወራ ዋጋ የለውም፡፡ ስለኪራይ ሰብሳቢነት ለ20 ዓመታት ስናወራ ነበር፡፡ ይህ ጎተራችንን የማይሞላ ከሆነ ምን ይጠቅማል? ከአሁን በኋላ መንቃት አለብን፡፡ ያለፈውን ታሪክ እንቀይር፤›› የሚል ቀስቃሽ ንግግር አድርገው ነበር፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy