Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አዲስ የተገኘው የጡት ካንሰር መድሃኒት ከ5 ተጠቂዎች 1 እንደሚያድን ተገለፀ

0 1,009

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ተመራማሪዎች የመፈወስ አቅሙ ሻል ያለ እና ከአምስት የጡት ካንሰር ተጠቂዎች አንድ መታደግ የሚችል መድሃኒት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።በአሁኑ ጊዜ በባዮሎጂካል ቴራፒ የሚሰጠው ህክምና የጡት ካንሰር ጉዳትን ለመቀነስ በብቸኝነት በመሰጠት ላይ የሚገኝ አማራጭ ነው።ሆኖም ግን ተመራማሪዎች አዲስ አገኘነው ያሉት የጡት ካንሰር መድሃኒት በርካታ ሴቶችን እንደሚጠቅም አስታውቀዋል።እንደ ተመራማረዎቹ ግምትም አዲሱ መድሃኒት ከአምስት የጡት ካንሰር ተጠቂዎች አንድ ተጠቃሚ ያደርጋል።

በመድሃኒቱ በእንግሊዝ ብቻ 10 ሺህ የሚደርሱ ሴቶች በየዓመቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት።መድሃኒቱ በአሁኑ ጊዜም BRCA1 ወይም BRCA2 ዘረ መል ላላቸው ሴቶች በመሰጠት ላይ መሆኑንም ነው የገለጹት።በባዮሎጂካል ህክምና (ቴራፒ) BRCA በመባል በሚጠራው ዘረ መል (ጂን) ላይ በሚፈጠር ችግር የሚመጣን የጡት ካንሰር ለማከም የሚረዳ ነው።

ትረስት ስትሬንጀር ኢኒስቲቲዩት አዲስ በሰራው ጥናት ያገኘው መድሃኒት ግን ከዚህ የዘረ መል (ጂን) ችግር ውጭ የሚከሰት የጡት ካንሰርን ለመቆጣጣር የሚረዳ ነው ተብሏል።በጥናቱ ላይ ተመራማሪዎች የ560 የጡት ካንሰር ተጠቂዎችን ዘረ መል ላይ ጥናት አድርገዋል።

በጥናታቸውም አብዛኛው የጡት ካንሰር ተጠቂዎች BRCA1 ወይም BRCA2 ዘረመል (ጂን) ላይ በሚፈጠር ችግር ከሚመጣ የጡት ካንሰር ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ለይተዋል።በዚህም ከአምስት የጡት ካንሰር ተጠቂዎች አንዱ ፒ.ኤ.አር.ፒ ኢኒሂቢተር (PARP inhibitor) ከተባለው መድሃኒት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy